
ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በቦታው እንዳልነበርና የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ የገባው የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር መጋጨቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በሰጡት መግለጫ አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት የሱዳን ሠራዊት የኢትዮጵያና የሱዳን ህዝብ ታሪካዊ ወዳጅነትን በማይመጥን መልኩ በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ወረራ መፈጸሙን ጠቅሰዋል።

የሱዳን መከላከያ ኃይል በተለያየ ጊዜ ውስጣዊ ችግሮች ባጋጠሙ ቁጥር በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳዎችን ሲያደርግ መቆየቱንም ነው ያነሱት።
ከሰሞኑም የሱዳን ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት በአካባቢው በነበሩ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ላይ ጥቃት ማድረሱንና ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
ይህ ሆኖ እያለ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በስፍራው ባልነበረበት ሁኔታ ምርኮኞችን ገደለ በሚል የሱዳን ጦር ክስ ማቅረቡ ተቀባይነት የሌለውና መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በቦታው አልነበረም ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፤ ምርኮኞችን ቢይዝ እንኳን ሕግ አክባሪነት፣ ሕዝባዊነትና ግዳጅ አፈፃፀም የሠራዊቱ መለያ ባህርያት ናቸው ነው ያሉት።
የሠራዊቱ ዲሲፕሊን በኮሪያና በኮንጎ ዘመቻዎች ጭምር የተመሰከረለት መሆኑን ጠቅሰው በሁለቱ ሱዳኖች የአብዬ ግዛት እንኳን በሥነ ምግባሩ እንደተወደሰም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ሠራዊት ከመንግሥት ትዕዛዝ ሳይሰጠው የሚንቀሳቀስ ሳይሆን በጥብቅ የዕዝ ሰንሰለት የሚመራ ነው ብለዋል።
የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ማጣራት የሚፈልግ አካል ካለ ከሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንዲጣራ ለመተባበር የኢትዮጵያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
