
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በክልሎች መካከልና በክልሎች ውስጥ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ያስችላል የተባለለት የብሔራዊ ግጭት መከላከልና ሰላም ግንባታ ስትራቴጂ ሰነድ በፌደሬሽን ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለውይይት ቀርቧል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ብሔርንና ማንነትን መሰረት ያደረጉ፣ ከወሰንና ማንነት ጋር የተያየዙ ግጭቶች እየተከሰቱ በርካቶችም እየተጎዱ በመኾኑ ሰነዱ እንዲዘጋጅ ምክንያት እንደሆነ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል።
ዘላቂ ሰላም ለመገንባትና ዜጎች የሚያምኑበት ዴሞክራሲ ለመተግበር የሚቻልበትን አግባብ ባመላከተ መልኩ ሰነዱ መዘጋጀቱንም አፈጉባኤው ገልፀዋል።
የሰነዱ ዝግጅት ጊዜ ወስዷል ያሉት አቶ አገኘሁ፤ የተቋማት መገፋፋት ሰነዱ በፍጥነት ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዳይገባ ማድረጉንም አንስተዋል።
የብሔራዊ ግጭት መከላከልና የሰላም ግንባታ ስትራቴጅ ሰነድ ወደ ተግባር ሲገባ የታለመለትን ተልዕኮ እንዲወጣ የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል ተብሏል።
ኢብኮ እንደዘገበው በሰነዱ ዙሪያ ከፌደራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
