የትውልድ የሙግት ገጾች …

22

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 7/2012 ዓ.ም (አብመድ) ያልተሰወረው እውነታ ኑረን ያልደረስንባቸው፣ የኖርናቸው፣ የነበሩን የሕይወት ገፆች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ የሠላም ደሴት ናት፡፡ በልዕለ ኃይል ተራዳኢነትም ሆነ በሰው ልጆች የተባበረ አንድነት እንደ ኢትዮጵያ ስለሠላም ማስተማር የሚችል አይኖርም የሚሉ እሳቤዎችም ይደመጣሉ፡፡ ሠላም ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ሁሉ ወደፊት እንዲኖሩ እጅግ ቀዳሚው የኅልውና ጉዳይ ነው፡፡ ኅልውናን የሚያስቀጥለውን ጉዳይ በዕውቀትም ሆነ በልምድ ተፈትኖ እንዲኖር ማስቻል ምንም ፖለቲካዊ ይዘት የለውም፡፡

በባሕር ዳር ከተማ አብመድ ተዟዙሮ ያነጋገራቸው ሰዎች ‹‹ሠላም ከሌሎች የምንጠብቀው ተአምራዊ ኃይል ሳይሆን ሁሉም የበኩሉን ከማድረግ የሚገኝ የጋራ ጥቅም ነው›› ብለውም ያምናሉ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪው አቶ ይስሐቅ ወንድማገኝ ‹‹ሁከት አንድን ጉዳይ በሠላም ለማግኘት አለመቻል ውጤት ነው›› ብለዋል፡፡

አቶ ይስሐቅ እንደተናሩት ኢትዮጵያውያን የሠላም እሴት ዓውድ ናቸው፤ ኢትዮጵያም ብዝኃነትን ያለምንም ችግር በፍቅር አስተሳስራ የኖረች በዚህም የጋራ ትልልቅ ታሪኮችን ያስመዘገበች ሀገር ናት፡፡ ወደኋላ በተውናቸው ዘመናት ኢትዮጵያ ውስጥ ሠላም ሲደፈርስ የነበረው በፖለቲከኞች ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ በሚደረግ ግብ ግብ፣ ከዕውቀት ማነስ በተፈጠሩ ስህተቶች፣ በፍትሕ ሥርዓቱ አለመዘመን እና ተቀራርቦ ባለመነጋገር እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ ‹‹ከዚህ ውጭ በየትኛውም ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ ከሕዝብ ሴራም ሆነ ጥላቻ አልነበረውም፤ አሁንም ለዚህ የሚጋብዝ ምልክት የለም›› ብለዋል አቶ ይስሃቅ፡፡

ኢትዮጵያ የሠላም ደሴት ስለመሆኗም ከጥንት እስከ ዛሬ ማጣቀሻ ይሰጣሉ፡፡ ‹‹ምድር ከጥፋት ውኃ በኋላ ስትነቃ የኖህ መርከብ ማረፍያ በመሆን የሠላም መሠረት ነበረች፡፡ በኋላም ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በመሆን ሠላም ከጠፋባቸው ሀገራት ሁሉ ተለይታ ሠላም የሰፈነባትን ኢትዮጵያን መርጣ በሠላም ኑራለች፡፡ ነብዩ ሙሀመድም ኢትዮጵያ የሠላም መገኛ መሆኗን በማወቃቸው ወገኖቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ አድርገው በሠላም እንዲኖሩ አድርገዋል፡፡ ነጮች መላው ዓለምን በቅኝ ግዛት ስስት በማየታቸው ሞትና ጩኸት ሲበረታ ኢትዮጵያውያን በአንድነታቸው የማያውቁትን የቅኝ ተገዥነት ማቅ አውልቀው ጥለዋል፡፡ ዜጎች ሠላማቸውን በተባበረ ክንድ እንዲያገኙም ምሳሌ ብቻ መሆን ሳይሆን በዕውቀትም የምታግዝ ሀገር ሆናለች፡፡ ይሄ የሠላም ተምሳሌትነት አሁን ላይ ዜጎች ውስጥ እንዲኖርም ለሰው ልጆች ሁሉ እኩል የሚያስተሳስብ በጎ ኅሊናና ምቹ አስተዳድር መፍጠር ያስልገናል›› ብለዋል፡፡

‹‹በሠላም ለመኖር ያለመቻል የልዕለ ተፈጥሮን ስጦታ በኃይል የሚገረስስ የሰው ልጆች የጨለማ ገጽ ነው›› ያሉት ደግሞ ሌላው የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ አቶ አሸናፊ ሺዋንግዛው ናቸው፡፡ ሠላምን የሚያደፈርሱ ስውር የቤት ሥራዎች ውጤት አሁን ሕዝቡ ያለውን የኑሮ ደረጃ የከፋ እንዳደረገው እንደሚያምኑም ነግረውናል፡፡

አቶ አሸናፊ “በወቅቱ ያልተፈፀሙ የጥላቻ ትርክቶችን መርጨት፤ በሂደት የወረስነውን ድህነት መገለጫ አድርጎ የአሁኑ ትውልድ አጀንዳ መሆኑ የወደፊት ጉዞችንን አስፈሪ ያደርገዋል፡፡ ያልኖርነውን ታሪክ ለማስተካከል ሌላ ታሪክ ከማበላሸት ወይም ሌላ አዲስ ልቦለድ ታሪክ ከመድረስ ለምንኖረው ነገ ታሪክ ፍኖተ ካርታ መገንባት ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

ትውልድ በሚያመጣው ሐሳብ ዕድገት ይለካል፡፡ የሐሳብ የበላይነት እንዲኖር ሠላምን የሁሉም መሠረት ማድረግ እንደሚያስፈልግም መክረዋል፡፡ በመንፈሳዊ ተጋድሎ እና ትሩፋቶች ውስጥ ያለውን ዕውቀት ሕዝባዊ ዕድገት ሁኖ እንዲመዘገብ የትውልድ የሙግት ገፆች መፍትሔ አመላካች መሆን እንዳለባቸው ነው የተናገሩት፡፡

የሀሰተኛ ትርክት መነሻውን ለመመርመር በማንበብ፣ በመረዳት፣ በመጠየቅ ለእርምት ትግበራው መሠረት መጣል እንደሚገባም አቶ አሸናፊ አሳስበዋል፡፡

ዶክተር ታደሰ ብሩ ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሑፍ (2013 እ.አ.አ) ‹‹ሠላም ምንድን ነው? ሠላም ማለት የሁከት አለመኖር ማለት ነው?” ይላሉ፡፡ ዶክተር ታደሰ የሠላም ተቃራኒው ሁከት ነው የሚል ቀጥተኛ ትርጉሙን መንገራቸው እንጂ የዓለምን የተቃርኖ ገጾች ውጤት ሂደት ‹‹ ካልደፈረሰ አይጠራም›› የሚለውን ረስተው አይደለም፡፡ ሠላም ሁከት አለመኖር ማለት አይደለም፡፡ ይህ ብዙዎች እንዲኖራቸው የሚፈልጉት ነገር ግን ተፈጥሯዊ ያልሆነ ሐሳብ ነው፡፡ ይህንን ሐሳብ የሚያጠናክር የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ

Previous articleየኔዘርላንድ ባለሀብቶች በአማራ ክልል በአበባ ልማት ሊሰማሩ ነው፡፡
Next article“ከ139 የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድም ሴት የፓርቲ መሪ የለም:” ወይዘሮ ሳባ ገብረ መድህን- የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዳይሬክተር