
ሰኔ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በንጹሐን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያና ፍጅት አውግዟል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባዔ ተቋማት ከሰሞኑ በወለጋ፣ በጋምቤላ እና በሌሎች አካባቢዎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የተፈፀሙትን ኢ – ሰብዓዊ ግድያዎችና ፍጅቶች በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡
ጉባዔው በንጹሐን ዜጎች ህልፈተ ሕይወት ሐዘኑን ገልጿል። ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ተመኝቷል፡፡ በጥቃቱ የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት የደረሠባቸው ወገኖችን ከጉዳታቸውና ከቁስላቸው እንዲፈውሱ በጸሎታችን እናስባቸዋለንም ነው ያለው፡፡
በኢትዮጵያ የሚታየው የሃይማኖት ማንነትንና የብሔር ውግንናን መሠረት በማድረግ የሚፈፀመው ጥላቻ፣ ማፈናቀል፣ ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ ግድያና ፍጅት እየተባባሰ ከመሄዱም በላይ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት እንደኾነ መቀጠሉ በእጅጉ የሚያሳስብ ነውም ብሏል፡፡ በኢትዮጵያዊያን መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር በማድረግ ሀገራዊ አንድነትን የሚሸረሽር የወንጀል ድርጊት እንደኾነ ጉባዔያችን ይገነዘባል ነው ያለው፡፡
በንጹሐን ላይ የተፈፀመው ግድያ ወንጀል ከመኾኑም በላይ ድርጊቱ ንጹሐንን የማሸበር ተግባር በመኾኑ መንግሥት በዘላቂነት የሕዝቡን ደኅንነትና ሰላም የማስጠበቅ መንግሥታዊ ኀላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠይቋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/