የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሕግ ማስከበር እና የህልውና ዘመቻውን በማገዝ በኩል የነበረው ሚና ከፍተኛ እንደነበር በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ተናገሩ።

202

ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደ ሀገር የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመገንባት በተደረገው ርብርብ የራሱን አስተዋጽኦ እንደተወጣ ጠቁመዋል።
ኮሎኔል ጌትነት ኢትዮጵያ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የጥፋት ድግስ በተደገሰላት እና በተወረረችበት ወቅት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሕዝቡን በማነቃነቅ ጠላቱን እንዲለይ እና የመጣበትን ወራሪ እንዲመክት የራሱ አስተዋጽኦ ነበረው ብለዋል።
ኮሎኔል ጌትነት ሕዝቡ አመራሩ እና ሠራዊቱ ጠላቱ ማን እንደኾነና ማንን መቃዎም እንዳለበት ሚዲያው በጎ ተግባር ፈጽሟል ነው ያሉት።
ሚዲያው ሀገር ወዳዱን የጸጥታ አካል በማነቃነቅ በኩልም ሚናው ከፍተኛ መኾኑን ተናግረዋል።
ሠራዊቱ ከሕዝቡ ጋር ያለውን ቁርኝት እንዲያጠናክር፣ ወገን እንዲደራጅ እና እንዲዘጋጅ በማድረግ በኩልም ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ የሠራው መልካም ተግባር አሁንም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጠላትን ከፋፋይ አጀንዳ እና ጅምላ መቃብሮችን በማጋለጥ፣ ወራሪው ቡድን በመንግሥት እና በግለሰቦች ንብረት ላይ ያደረሰውን ጉዳት ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር በመተጋገዝ አጋልጧል፣ ሕዝቡ ተደራጅቶ ሠራዊቱን እንዲያግዝ በማድረግ በኩልም ኃላፊነቱን በአግባቡ የተወጣ ሚዲያ ነው ብለዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጠላት የተካነበትን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ በማክሸፍ እና እውነቱን በማጋለጥ በኩል የሄደበት ርቀት ይበል የሚያሠኝ እና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ መኾኑን አሳስበዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአውደ ውጊያ ዘገባዎችን በተሻለ መንገድ መሥራቱንም አንስተዋል።
ሕዝቡን የመረጃ ተጠቃሚ በማድረግ ወጣቶች የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ መከላከያው ስብጥሩን ጠብቆ እንዲደራጅ በማድረግ በኩል ኮርፖሬሽኑ ውጤታማ ሥራ የሠራ ቢኾንም አሁንም ቀሪ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
አማራ ክልል የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ከመኾኑ ጋር ተያይዞ ብዙ ይጠበቃል ያሉት ኮሎኔል ጌትነት ሠራዊቱ ግዳጁን በአግባቡ እንዲወጣ ሚዲያው ይህን አጠናክሮ መሥራት አለበት ብለዋል።
ጠላት ማኀበራዊ ሚዲያውን ተጠቅሞ መከላከያ ሠራዊትን ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ አብረው ሲተቹ የነበሩ ሚዲያዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ኮሎኔል ጌትነት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ይህን በማጋለጥ፣ ወቅታዊ መረጃ ለማኅበረሰቡ በማድረስ የድርሻውን እንደተወጣ ጠቁመዋል።
ሀገርን እንደ ሀገር ለማስቀጠል የመከላከያ ሠራዊት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት እና የሀገርን ሉዓላዊነት የሚያስከብርበት ቁመና እንዲኖረው ጠንክሮ መሥራት እንደሚገባውም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ትርንጎ ይፍሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሚኮ ኅብር የሕዝብ አንድነት፣ መቻቻል፣ ፍቅርና ሕብረ ብሔራዊነት እንዲለመልም አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት የሀገሪቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን የሥራ ኀላፊዎች ተናገሩ፡፡
Next articleበአሸባሪው ሸኔና በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል የወደሙ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን መልሶ እየገነባ መኾኑን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ገለጸ።