አሚኮ ኅብር የሕዝብ አንድነት፣ መቻቻል፣ ፍቅርና ሕብረ ብሔራዊነት እንዲለመልም አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት የሀገሪቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን የሥራ ኀላፊዎች ተናገሩ፡፡

154

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱንና ተደራሽነቱን በማስፋት እንዲኹም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ኅብረተሰቡን እያገለገለ ይገኛል። ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ሚዲየሞቹ በ10 ቋንቋዎች በማሰራጨት ኅብረ ብሔራዊነቱን እያስመሰከረ ነው።
አሚኮ ዛሬ ሰኔ 13/2014 ዓ.ም “ኅብር” የተሰኘ ሁለተኛውን የቴሌቪዥን ቻናል በይፋ የማስጀመር መርኃግብር አካሂዷል። በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ የሀገሪቱ የሚዲያ የሥራ ኀላፊዎች ታድመዋል።
የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌትነት ታደሰ የአማራ ክልል ሕገመንግሥት በክልሉ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችን መብት የሚያከብር እንደኾነ ተናግረዋል። አሚኮም የክልሉ ሕገመንግሥትን በማንጸባረቅ ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል። “አሚኮ ዛሬ በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች ተደራሽ ኾኗል፤ አሚኮ የኢትዮጵያን ሕዝብ መልክ ይዞ ወጥቷል” ብለዋል።
ሚዲያዎች የሕዝቡን የጋራ እሴት በማጠናከር የእርስ በርስ ግንኙነቱ እንዲጎለብት እንዲሠሩም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠይቀዋል።
የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ገቢሳ አሚኮ በ10 ቋንቋዎች ሥርጭት መጀመሩ በሀገሪቱ ትልቅ አሻራን እንዲያሳርፍ አድርጎታል ብለዋል። አሚኮ ኅብር በኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ አንድነት፣ መቻቻል፣ ፍቅርና ሕብረ ብሔራዊነት እንዲለመልም አይነተኛ ሚናን ይጫወታል ነው ያሉት።
አሚኮ የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሕዝቡን ማኅበራዊ እሴት እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ አይተኬ ሚናን ይጫወታል። አሚኮ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የሚኖሩ ሕዝቦችን የማቀራረብ ተግባርን እየፈጸመ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል። ሚዲያዎች የተሳሳተ ትርክትን በማስቀረትና የሕዝብን አንድነት በማስጠበቅ በኩል ተግተው ሊሠሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ሰናይት ሰለሞን አሚኮ የክልሉም ኾነ የሀገሪቱ ድምጽ በመኾን ትልቅ መሳሪያ ኾኖ እያገለገለ ይገኛል ብለዋል። አሚኮ ለሌሎች ሚዲያዎችም አርዓያ የመኾን ተግባርን ፈጽሟል ነው ያሉት።
አሚኮ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ጠንክሮ እየሠራ ነው ያሉት ደግሞ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ሀብቴ ናቸው። አሚኮ በ10 ቋንቋዎች ሥርጭት መጀመሩ የተሳለጠ መረጃ ልውውጥ እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“አሸባሪዎችን እና ጽንፈኞችን ለሕግ የማቅረብ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Next articleየአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሕግ ማስከበር እና የህልውና ዘመቻውን በማገዝ በኩል የነበረው ሚና ከፍተኛ እንደነበር በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ተናገሩ።