“አሸባሪዎችን እና ጽንፈኞችን ለሕግ የማቅረብ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

196

ሰኔ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በፀጥታ አስከባሪ አካላትና በሕዝቡ የተባበረ እርምጃ በአሸባሪውና ፅንፈኛው ሸኔ ቡድን ላይ በደረሰበት ሽንፈትና ኪሳራ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡
በቅርብ ጊዜ በጋምቤላ አካባቢ ያደረገው ሙከራ ሲከሽፍበት በምዕራብ ወለጋ በጊምቢ አካባቢ ደግሞ በንጹሐን ዜጎች ላይ በተለይም በሕጻናትና በሴቶች ላይ ያካሄደው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ እና ኢሰብዓዊ ነው ብለዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪ ቡድኑ በወሰደው እኩይ የጥፋት እርምጃ ምክንያት በንጹሐን ወገኖች ላይ ለደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።
በመንግሥት በኩል ሕግ የማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ ነው ያሉት።
በቀጣይ ተጎጂ ቤተሰቦችን የማረጋጋት፣ የመደገፍ እና መልሶ የማቋቋም ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ የገለጹት አቶ ደመቀ አሸባሪዎችን እና ጽንፈኞችን ለሕግ የማቅረብ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleእድልን መጠቀም ፈተናን ደግሞ ማለፍ ግድ እንደሚል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ፡፡
Next articleአሚኮ ኅብር የሕዝብ አንድነት፣ መቻቻል፣ ፍቅርና ሕብረ ብሔራዊነት እንዲለመልም አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት የሀገሪቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን የሥራ ኀላፊዎች ተናገሩ፡፡