
አዲስ አበባ: ሰኔ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመጀመሪያው የቻይና አፍሪካ ቀንድ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በኮንፈረንሱ የቻይና የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዡ ቢንግ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን እና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት አምባሳደሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ተወካዮች ተገኝተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ጉባኤ በማዘጋጀቷ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው የቀንዱ ሀገራትን ሰላም ማረጋገጥ የሚቻለው ሀገራቱ ባለቤትና ተከላካይ መኾን ሲችሉ ነው ብለዋል። “አካባቢውን ማልማት እና ሰላማዊ ማድረግ የእኛ ኀለፊነት ሲኾን ጊዜው ደግሞ አሁን ነው” ብለዋል።
የቻይና የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ዡ ቢይንግ “የቻይና ፕሬዝዳንት እኔን መልእክተኛ አድርገው ሲልኩ ቀጠናውን ሰላም ለማድረግ ለመተባበር እና ለመተጋገዝ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል” ብለዋል።
ምሥራቅ አፍሪካ በተፈጥሮ ፀጋ የታደለ በመኾኑ አካባቢውን ለማልማት እና ለማሳደግ ካለፈው ስህተት ተምሮ የዛሬውን እድል መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
ቻይና በአፍሪካ ውስጥ በርካታ ፍብሪካዎችን፣ የልማት ማዕከላትን፣ የጤና ተቋማትን እና የትምህርት ተቋማትን የገነባች መኾኑን ያስረዱት ልዩ መልእክተኛው ይህንን ትብብር ወደፊት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስገንዝበዋል፡፡
በኮንፈረንሱ የሁሉም የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ተወካቶች፣ ሚኒስትሮች እና አምባሳደሮች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/