❝በቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልሎች ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር በኾነ አካላት የተፈጸመው የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት የምንታገሰው አይደለም❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

151

ሰኔ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በንጹሐን ዜጎች ላይ በሕገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና መተዳደሪያን ማውደም ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልሎች፣ ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር በሆነ አካላት የተፈጸመው የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት የምንታገሰው አይደለም ነው ያሉት። ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደኅንነትን መመለስ አሁንም ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባራችን ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“አሚኮ የጣቢያዎቹን ቁጥር እያሳደገ የአገልግሎት አይነቱን እያሰፋ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን እና ወንድማማችነትን ለማስረጽ ድርሻውን እየተወጣ ይገኛል” የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥዬ
Next articleየአሚኮ ኅብር መጀመር መረጃ ከመስጠት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ትርጉም እንዳለው ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡