“የተቀመሩትን የባንኩን እሴቶች በማጉላት በፋይናስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ገበያውን በመቀላቀል የኢንዱስትሪ ጉልበት ለመኾን እንሠራለን” የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ

374

ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ባንክ የሥራ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ አማራ ባንክ የተቀናጁ ሀሳቦች፣ የተባበሩ እጆች የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውጤት ኾኖ የተቋቋመ ባንክ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ባንኩ እንዲመሰረት የኅብረተሰቡ ጉጉት ከፍተኛ እንደኾነም ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው የገለጹት፡፡
የሕዝብን ፍላጎት እውን ያደርግ ዘንድ አማራ ባንክ የካቲት 2/2014 ዓ.ም ፈቃድ በማግኘት ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ሥራዉን በይፈ ጀምሯል ብለዋል፡፡
ባንኩን ሥራ ለማስጀመር ውጣ ውረድ እንደነበረ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ባንኩ የታለመለትን ዓለማ ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡
የተቀመሩትን የባንኩን እሴቶች በማጉላት በፋይናስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ባንኩ ቃሉን ከተግባር ጋር የተገናኘ እንዲኾን በሙሉ ልብ ገበያውን በመቀላቀል የኢንዱስትሪ ጉልበት ለመኾን እንሠራለን ነው ያሉት፡፡
የቦርድ አባላት፣ የባንኩ ባለአክስዮኖችና ሠራተኞች ከባንኩ ጎን መቆም እንዳለባቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
“የአማራ ባንክ መከፈት ዋነኛ ዓላማ ሀገሪቱ የጀመረችውን ልማት ማፋጠንና በባንኩ ዘርፍ ምሳሌ መኾን የሚያስችል ስትራቴጂን በመቅረጽ ለሠራኞች ተገቢውን ስልጠና በመስጠት ተገቢውን ድልድል በማጠናቀቅ ዛሬ ዝግጁ ኾነናል” ብለዋል፡፡
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የሚከፈቱት 70 የባንኩ ቅርንጫፎች ከፍተኛ የግል የቁጠባ ሒሳብና ተቀማጭ ገንዘብ ለማሰባሰብ ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው እምነታቸው መኾኑን ገልጸዋል፡፡
“ከባንክ ባሻገር በሚል መለያ ወደ ሥራ የገባው የአማራ ባንክ ከጎኑ ለኾናችሁት ውድ ደንበኞቻችንን ለማገልገል ዝግጁ ነን፤ እንኳን ደስ አላችሁ” ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአማራ ባንክ የሥራ ማሥጀመሪያ ማብሰሪያ መርኃ ግብር ዛሬ ይካሄዳል።
Next articleአማራ ባንክ በፉክክር ሳይኾን በውድድር፣ በተናጠል ሳይኾን በውህደት በሌሎች ኪሳራ ሳይኾን አብሮ በማደግና በሀገር ልማት ላይ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ ተናገሩ፡፡