
እንጅባራ: ሰኔ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የሥራ ኀላፊዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡
“አዲስ የፖለቲካ ዕይታ፤ ለአዲስ ሀገራዊ እምርታ’’ በሚል መሪ መልዕክት በሦስት የሥልጠና ማእከላት እየተሰጠ ባለው ሥልጠና ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ ሠልጣኞች እየተሳተፉ ነው፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አለማየሁ ገበየሁ ሥልጠናው ከብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያው ጉባኤ ማግስት በሕዝብ ውይይት የተነሱ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን በብቃትና በቁርጠኝነት መመለስ የሚችል የሥራ ኀላፊዎችን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡
ኀላፊው ብልጽግና ፓርቲ ሀገርን ሊያሻግሩ የሚችሉ ትልልቅ እቅዶች እንዳሉት አንስተዋል፡፡ ፓርቲው ወደ መሪነት ሲመጣ በፈተና ውስጥ ኾኖም ቢኾን በርካታ ስኬታማ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል፡፡
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሀገራዊ ለውጥን ተከትሎ ከ50 በመቶ በላይ ተቋማት በአዳዲስ የሥራ ኀላፊዎች የተዋቀሩ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሥልጠናው የሥራ ኀላፊዎችን የመፈጸም አቅም በማቀራረብ የተቀመጡ እቅዶችን በስኬት ለማጠናቀቅ ትልቅ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ሥልጠናው ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ እያደገ የመጣውን የሕዝብ የመልማት ፍላጎት በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ምላሽ ለመስጠት እገዛ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/