ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተናገሩ፡፡

93

ሰኔ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምሥራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ዳይሬክቶሬት ጀኔራል አምባሳደር ኤሊፍ ኮሞሎኡ የንን በጽሕፈት ቤታቸዉ ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ያለዉን ወቅታዊ ሁኔታ፣ መንግሥት ለሰላም እያደረገ ያለውን ጥረት እና ፍላጎት አብራርተዋል። በተለይ በግጭቱ ምክንያት ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይከሰት፣ መንግሥት የምግብ አቅርቦት እና ድጋፍ እንዲኖር ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን እና ከዓለም የምግብ ፕሮግራም እንዲሁም ከረጂ አካላት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ መንግሥት ለሥራው ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል።

መንግሥት ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታት ለሰላም እና መረጋጋት ባለዉ ፅኑ ፍላጎት በአሁኑ ወቅት ተስፋ ሰጭ ጅምሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሸባሪው ሕወሓት በየጊዜው የሚያሳየዉ ተለዋዋጭ የኾነ አቋም የሰላም ጥረቱን ወደ ኋላ እየጎተተው መኾኑን ገልጸዋል።

በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምሥራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ዳይሬክቶሬት ጀኔራል አምባሳደር ኤሊፍ ኮሞሎኡ የን በበኩላቸው ቱርክ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መኾኗን ተናግረዋል፡፡ የሀገራቱ ግንኙነት በንግድ እና በኢንቨስትመንት እየጎለበተ መጥቷል ነው ያሉት፡፡ ኢትዮጵያና ቱርክ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚ መስኮች ትብብራቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በነዳጅ እና ማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ ልዑክ ጉብኝት እያደረገ መኾኑን እንዳመላከቱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በሰላም ለመፍታት እያደረገ ያለዉን ጥረት አድንቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፖሊስ የሥራ ኀላፊዎች ጋር መከሩ።
Next articleየውጭ ኃይሎች ተጽዕኖ እና ፍላጎት የሚንጠው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር