በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት በባህል ልውውጥም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጹ።

215

ሰኔ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አምባሳደር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ከቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ቲቦር ናጊ ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደሩ ለቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር እና ከቴክሳስ ቴክ ዩኒቨርሲቲ እና ከአንጀሎ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለተውጣጡ 15 ተማሪዎች በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ስላለው የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ገለጻ አድርገዋል።
ተማሪዎቹ ጋር ከተደረጉላቸው ውይይቶች በተጨማሪ የኢትዮጵያን ባህላዊ የቡና ሥነ ሥርዐት የመታደም እድል አግኝተዋል።
የተማሪዎቹ የጉብኝት መርኃግብር በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ መግባባትን እና የባህል ልውውጥ ለማጎልበት እንዲሁም ወዳጅነትን ለማጠናከር እንደሚረዳ መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleመንግሥት ጥፋተኛ የኾኑ ግለሰቦችን ለሕግ ሲያቀርብ ሕብረተሰቡ ሊተባበር እንደሚገባ ተጠቆመ።
Next articleበጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚዘጋጀው አዲስ ወግ ‘ከጽንፎች መሐል ወርቃማውን አማካይ ፍለጋ’ በተሰኘ ርዕስ እየተካሄደ ነው።