መንግሥት ጥፋተኛ የኾኑ ግለሰቦችን ለሕግ ሲያቀርብ ሕብረተሰቡ ሊተባበር እንደሚገባ ተጠቆመ።

114

ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የጀመረው ርምጃ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን መንግሥት አስታውቋል። የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተግባሩ ሕጋዊ ሥርዓቱን ጠብቆ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ነዋሪው አቶ እሱባለው ስንሻው መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አበረታች ነው ብለዋል። አቶ እሱባለው መንግሥት የሕግ የበላይነትን ሊያስከብር ሕዝቡም ሕግን ሊያከብር እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡ አስተያየት ሰጪው እንዳሉት የሕግ የበላይነት ሲከበር ሠርቶ መብላት ወጥቶ መግባት ቀላል ነው፤ ምክንያቱም አንዱ የአንዱን መብት አይነካም፤ ሁሉም ራሱን አውቆ፣ ሕግን አክብሮ መንቀሳቀስ ይችላል ነው ያሉት፡፡

መንግሥት ጥፋተኛ የኾኑ ግለሰቦችን ለሕግ ሲያቀርብ ሕዝቡ አጋዥ ሊኾን እንደሚገባ ነው አቶ እሱባለው የተናገሩት።

ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ሕዝቡ ለፀጥታ አካላት መረጃ በመሥጠትና ምስክር በመኾን ያላጠፉትም ያለአግባብ እንዳይጠየቁ ተባባሪ መኾን እንዳለበት አስተያየት ሰጪው ገልጸዋል።

የሕግ ጥሰት የሚፈጽሙ አካላት በውስጡ መኖራቸውንም መንግሥት ሊረዳ ይገባል ያሉት አስተያየት ሰጪው ሕዝብ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ የራሳቸውን የገቢ ምንጭ የሚያሯሩጡ አካላትን በአግባቡ ሊመረምር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የሕግ የበላይነት መረጋገጥ እንዳለበት የገለጹት ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ሙሉጌታ በለጠ ናቸው፡፡ አስተያየት ሰጪው ሕግ የማስከበሩ ሥራ በመጀመሩ በርካታ ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች እየቆሙ ነው ብለዋል። አቶ ሙሉጌታ ማኅበረሰቡ በተለያዩ ሁከት ፈጣሪዎች ሰላሙን አጥቶ ቆይቷል፤ ሰላሙን እየነሱት ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሕግ የበላይነት መከበር አለበት፤ ለዚኽ ተግባር ሕዝቡ ተባባሪ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ ሀገር የጉልበተኞች ሳትኾን የሰላማዊ ሰዎች ልትኾን ይገባል ነው ያሉት።

መንግሥት የሕግ የበላይነት ሲያስከብር ባልተገባ አካሔድ በንጹኃን ላይ ጉዳት እንዳያደርስ መጠንቀቅ እንዳለበትም ጠቁመዋል አቶ ሙሉጌታ።
አስተያየት ሰጪው አሁን ላለው የገበያ አለመረጋጋት እና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ መነሻው የሕግ አለመከበር እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ መንግሥት ሕዝቡ ሰላማዊ ኑሮውን ባግባቡ የሚመራበትን መንገድ መፍጠር እንዳለበትም ተናግረዋል።

ሌላው አስተያየታቸውን ያጋሩን አስር አለቃ ሉሌ ይገርማል ይባላሉ። አስር አለቃ ሉሌ መንግሥት የጀመረውን የሕግ የበላይነት የማስከበር ዘመቻ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።
ማንኛውም ሰው ከሕግ በላይ አይደለም፤ ሕግ ሲከበር ደግሞ ሕገወጥ ተግባር የፈጸሙ አካላት በሕግ ሊጠየቁ ግድ ነው፤ በአንጻሩ ደግሞ ጥፋት ሳይኖርባቸው ለእንግልት የተዳረጉ አካላት ካሉ መንግሥት አጣርቶ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ይገበዋል ብለዋል። አስርአለቃ ሉሌ ማኅበረሰቡ ተጠርጣሪዎችን ለሕግ አሳልፎ በመስጠት ረገድ ከመንግሥት ጎን መቆም እንዳለበትም ጠቅሰዋል።

ዘጋቢ:- ትርንጎ ይፍሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleእየተከናወነ የሚገኘው የሕግ የማስከበር ተግባር የአካባቢያቸውን ሰላም ማረጋገጡን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next articleበአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት በባህል ልውውጥም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጹ።