“የሸኔ የሽብር ቡድን እና ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በጋምቤላ ከተማ በድንገት ከፍተውት የነበረው ጥቃት ከሽፏል” ርእሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ

193

ሰኔ ዐ8/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሸኔ የሽብር ቡድን ራሳቸውን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር በማለት ከሚጠሩ ታጣቂዎች ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ከፍቶት የነበረው ድንገተኛ ጥቃት በጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ ጥረት መክሸፉን የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ።
ርእሰ መሥተዳድሩ ጉዳዩን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ታጣቂዎቹ ወደ ጋምቤላ ከተማ ሰርገው በመግባት የሕዝቡን ሰላም ለማወክና ለመዝርፍ ያደረጉት ሙከራ በክልሉና በፌዴራል የጸጥታ ኀይሎች የተቀናጀ ጥረት ከሽፏል።
የክልሉና የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎቹ ላይ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም አሁን ላይ የጋምቤላ ከተማ በሰላምና መረጋጋት ላይ ትገኛለች ብለዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመኾን ጥቃቱ እንዲከሽፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦም ርእሰ መሥተዳድሩ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የጸጥታ ኀይሉና ኅብረተሰቡ በቅንጅት እየሠሩ መኾናቸውንም ተናግረዋል።
በከተማዋ አሁን ላይ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በስተቀር ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ የማይቻል ስለመኾኑም ገልጸዋል።
ኀብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና የትኛውም አይነት አጠራጣሪ ጉዳይ ሲገጥመው ደግሞ በአቅራቢያው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግ ርእሰ መሥተዳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌሎች አካባቢ የሚገኙ የክልሉ ነዋሪዎችም ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አካባቢያቸውን ነቅተው እንዲጠብቁ ጠይቀዋል።
የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በከተማዋ በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ላደረሱት የህይወት ጉዳትም ርእሰ መሥተዳድሩ በክልሉ መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአማራ እና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡
Next articleየአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ኅብር የቴሌቪዥን ቻናል መጀመር ኢትዮጵያዊ አንድነትን እና አብሮነትን እንደሚያጎለብት የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ የሽጥላ ተናገሩ።