
አዲስ አበባ: ሰኔ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአማራ እና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የዊልቸር እና የክራንች ድጋፍ አድርጓል።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በአማራ ክልል የተጠናከረ የሥነ ልቦና ድጋፍ ጭምር እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ በአማራ ክልል ጦርነቱ በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት ያደረሰ ቢኾንም የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳት የከፋ መኾኑን አስረድተዋል።
የተገኘውን ድጋፍ ለተጎጂዎች በአግባቡ ለማድረስ እንደሚሠሩም አስታውቀዋል። “ችግሩ በጣም ብዙ ነው፤ ተባብረን ከሠራን ከችግር መውጣት እንችላለን” ነው ያሉት። ኀላፊዋ አሁንም ድጋፍ ማድረግ የሚችል ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን በዘላቂነት ለመደገፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከአጋር አካላት ጋር ጥረት እያደረገ መኾኑ ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡-ዳንኤል መላኩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/