
ደሴ: ሰኔ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ እና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ላይ እንዲሁም ከነዳጅ አቅርቦት ሥርጭት ጋር በተያያዘ እያጋጠሙ ያሉ ወቅታዊ ችግሮችን በተመለከተ ለክልል እና ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች በደሴ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው።
ከነዳጅ ዘርፍ መሠረታዊ ችግሮች መካከል ዋነኛው ከዋጋ ጋር የተያያዘ ችግር ሲኾን በዚህ ረገድ ያለውን ችግር መፍታት የዘርፉን አብዛኞቹን ችግሮች መቅረፍ ተደርጎ ይወሰዳል። በዚህም መሠረት መንግሥት በቅርቡ ከዋጋ፣ ከታሪፍና ከትርፍ ሕዳግ ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በዚህ ውሳኔ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ እና በፓሊሲ ያልተደገፈውንና ሀገሪቷን ለከፍተኛ ዕዳ የዳረገውን ጥቅል ድጎማ ደረጃ በደረጃ በማስቀረት በሂደቱም አነስተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጎማ የሚደረግበትን መንገድ አመቻችቷል።
የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ እና ድጎማ አሰጣጥ ውሳኔ ዓላማ ከዓለም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የዋጋ ማሻሻያ ባለመደረጉ ምክንያት ሀገሪቱ ካጋጠማት ከፍተኛ የዕዳ ጫና መውጣት የምትችልበትን እና በሂደቱም የኅብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መፍትሔ መስጠት ነው። የሥራ ኀላፊዎቹ እና ባለሙያዎቹ በዘርፉ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን – ከደሴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/