የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር በድብቅ ድርድር እያደረገ ነው የሚለው ወሬ ሐሰተኛ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታወቁ፡፡

218

ሰኔ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሕዝብ ተወካዮች 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለምክር ቤት ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የድርድር ጉዳይ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማንም ጋር ሰላም እንፈልጋለን፣ ከሰላም ብዙ ነገር እናተርፋለን ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ድርድር ጀምሯል የሚባለው ወሬ ሐሰተኛ መኾኑንም አስታውቀዋል፡፡
ድርድር ካለ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የማወቅ መብት አለውም ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደፊት እንዴት መሄድ አለባት የሚለውን ብልጽግና ፓርቲ በሥራ አስፈጻሚው አማካኝነት ኮሚቴ አቋቁሞ እየሠራ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው ኮሚቴ ኢትዮጵያ የምትፈልገውን፣ ምን ሲሳካ ነው የምንነጋገረው? እንዴት ነው የምንነጋገረው? የሚለውን የሚያጠና መኾኑንም አስታውቀዋል፡፡ ኮሚቴው በጥናት ላይ መኾኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥናቱ ውጤት ሲቀርብና በውጤቱ መሠረት ቀጣይ ሊደረግ የሚችል ጉዳይ ሲኖር ለሕዘቡ ይፋ እንደሚኾንም ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ሕወሓት የአማራ ጠላት ሳይኾን የኢትዮጵያ ጠላት ነው ብለዋል፡፡ አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ብቻ የሚቆም አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ጠላት ነው፤ በጋራ እንታገለዋን ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ሰላም ወዳድ እንደኾነም ገልጸዋል፡፡ ለጥይት የምናወጣውን ለልማት እናውለዋለን ነው ያሉት፡፡ ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን ግን የተደበቀ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“በኮሮና ወረርሽኝና በጦርነት ውስጥ ኾነንም ባለፉት ሦስት ዓመታት በመንገድ ግንባታ አስደማሚ ሥራ ተሠርቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleበነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ እና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም በተመለከተ ለሥራ ኀላፊዎች እና ለባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡