
ባሕር ዳር: ሰኔ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር እየተገነቡ ያሉ መሰረተ ልማቶች አፈጻጸም ደረጃ በከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች ምልከታ እየተካሄደ ነው፡፡
ምልከታው መነሻውን በዓባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የአዲሱ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ አድርጓል።
•ድልድዩ ከፌዴራል መንግሥት በተመደበ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እየተገነባ ነው።
•ግንባታው 65 በመቶ መድረሱ ተነግሯል።
•በመጭው መጋቢት 2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
•ለዚሁ ድልድይ ግንባታ መዳረሻ የሚሆን የ4 ነጥብ 7 ኪ.ሜ የአስፋልት መዳረሻ መንገድ ሥራም በመፋጠን ላይ ነው።
በባሕር ዳር ከተማ የዓባይ ድልድይ ግንባታን ጨምሮ ሌሎች የመንገድ ሥራዎች፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው በፍጥነት ወደ ሥራ መግባት የቻሉ የእምነበረድና የብረታብረት ፋብሪካዎች የጉበኝቱ መዳረሻዎች ናቸው ተብሏል።
በከተማ አሥተዳደሩ ብቻ 8 መቶ ሚሊየን ብር ወጭ የኾነባቸው የአስፋልት እና የኮብል ስቶን የመንገድ ግንባታዎች እየተጎበኙ ነው። መንገዶቹ በአጠቃላይ ከ11 ኪሎሜትር በላይ የሚሸፍኑ ናቸው ተብሏል።
ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/