
ባሕር ዳር: ሰኔ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት ባለፉት አራት ዓመታት የተከሰቱ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ለማሳካት የታሰበውን ዕቅድ በታሰበለት ልክ እንዳይሄድ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ፈተናዎችን በሚገባ በመረዳት ሁኔታዎችን በትክክል መገንዘብ ጠቃሚ እንደኾነም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሪፎርም በፊት ኮሮናን ጨምሮ ሰው ሰራሽ ችግሮች ማጋጠማቸውን አብራርተዋል።
በሀገር ውስጥ ያጋጠመው ጦርነት ከፍተኛ የሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳስከተለም ተናግረዋል። ጦርነቱ ሀገር ለማፍረስ ታቅዶ የተጀመረ በመኾኑ ጉዳዩ በቀላሉ የሚታይ እንዳልኾነ ነው ያስገነዘቡት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩን ለመቀልበስ እና ኢትዮጵያን ለማዳን የተሠራው ሥራ በቀላሉ የሚታይ እንዳልኾነ ነው የጠቀሱት፡፡
ኢትዮጵያን ማፍረስና ታሪክ ማድረግ ከፈለጉ ኃይሎች ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ተገብቶ በአሸናፊነት መወጣት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሳትፈርስ የብልጽግና መሰረቷን እየጣለች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገጠመው ችግር ትምህርት ተወስዶ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
በምስጋናው ብርሃኔ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/