
👉 በባለፉት ሦስት ዓመታት 2 ሺህ 150 ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል፡፡
👉 የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ከመዋእለ ሕፃናት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የሚያካትት ነው።
👉 ከ15 ሺህ በላይ የማስፋፊያ ግንባታዎች በመከናወናቸው ተማሪዎች ሳይጣበቡ እንዲማሩ አስችሏል፡፡
👉 በትምህርት ቤት ምገባ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተማሪዎች በነጻ ምግብ ያገኛሉ፡፡
👉የኑሮ ውድነትን በተመለከተ፦
👉 ባለፉት ስድስት ወራ መንግሥት 30 ቢሊዮን ብር በመመደብ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ሠርቷል ነው ያሉት፡፡
👉 ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ መንግሥት ከሕዝብ ትራስፖርት ውጭ የነዳጅ ድጎማን እንደሚያነሳም ነው የተናገሩት፡፡
👉 በኢትዮጵያ የመብራት፣ የውኃ፣ የነዳጅ እና ሌሎች ድጎማዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
👉የምርት እጥረትና የፍላጎት መጨመር፣ የንግድ ሥርዓቱ መዛባት፣ ምርት እያለ ማቅረብ አለመቻል፣ ግጭትና የገንዘብ አጠቃቀም ጉድለት ለኑሮ ውድነቱ ዋና ምክንያት እንደኾኑም አብራርተዋል፡፡
👉 በዓለም ደረጃ ያለውን የዋጋ ንረት መገንዘብ ተገቢ ነው፤ በበርካታ ሀገራት ከፍተኛ የዋጋ ንረት እንዳለም ጠቁመዋል፡፡
👉 በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት 33 በመቶ መኾኑን አስረድተዋል፡፡
👉 የኑሮ ውድነቱ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ለሚያገኙ ዜጎች አስቸጋሪ መኾኑን አንስተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/