በኢትዮጵያ አየር መንገድና በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡

100

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ፣ ጦርነትና ሌሎች ችግሮች እያሉ ለውጥ ላይ መኾናቸውን ነው ያብራሩት፦
👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለውጥ በፊት 100 አውሮፕላን እንደነበሩት ገልጸው፣ አሁን ላይ 135 መድረሱንም ተናግረዋል፡፡
👉 አየር መንገዱ ከለውጥ ወዲህ 35 በመቶ የአውሮፕላን እድገት ማሳየቱንም አስታውቀዋል፡፡
👉 ከለውጡ በፊት አየር መንገዱ 115 መዳረሻዎች እንደነበሩት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ላይ 127 መዳረሻዎች በዓለም ላይ እንዳሉት ገልጸዋል፡፡
👉 ከለውጥ በፊት 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለውጡ በኃላ 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ላይ እንደደረሰ ነው የተናገሩት፡፡
👉 ለውጥ ሲጀምር 6 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግድ የነበረው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ 22 ሚሊዮን መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ ነው ያነሱት፡፡
👉 የሌሎች ሀገራት አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከመንግሥት ድጎማ ሲደረግላቸውና ሲንገዳገዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ከመንግሥት ድጎማ ሳይደረግለት እድገት ላይ መኾኑን አንስተዋል፡፡
👉 38 ሚሊዮን ደንበኞች የነበሩት ኢትዮ ቴሌኮም 65 ሚሊዮን ደንበኞች ላይ መድረሱንም ገልጸዋል፡፡
👉 ኢትዮ ቴሌኮምን በተመለከተ፦
👉 33 ነጥብ 5 ቢሊዮን ትርፍ የነበረው ኢትዮ ቴሌኮም 55 ቢሊዮን ብር መድረሱንም አስታውቀዋል፡፡
👉 ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌ ብር አገልግሎትን በመልካም ሁኔታ እየተጠቀመ መኾኑንም አንስተዋል፡፡
👉 በኢትዮ ቴሌኮምና በኢትዮጵያ አየር መንገድ የታዩ ለውጦች መልካም ቢኾኑም አሁንም በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮ ቴሌኮም ላይ የሚታዩ ችግሮችን መፍታት አስፈላጊ እንደኾነም አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ሃሳቦችና ጥያቄዎች።
Next articleጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በኑሮ ውድነት እና በትምህርት ጉዳዮች የሰጧቸው ማብራሪያዎች፦