የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ሃሳቦችና ጥያቄዎች።

277

👉የኢትዮጵያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት የጀመሩትን ተቋማዊ ግንባታ አጠናክረው እንዲቀጥሉ፡፡
👉የመንግሥት በሀገሪቱ ሕግ የማስበር ዘመቻ መልካም ውጤቶች እየጠመዘገቡ ነው፡፡ የሕግ ማስበሩ ዘመቻ የኅበረሰቡን የሕግ ይከበርልን ጥያቄ እየመለሰ ስለሆነ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
👉በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች እየተወሰዱ ያሉ የሕግ ማስከበር እርምጃዎች ተገቢውን የሕግ ስርዓት ያልተከተሉ መሆናቸውን ሕዝቡ እየገለጸ ነው፡፡
👉በሕግ ማስከበሩ እርምጃ በተፈጠሩ ግጭቶች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት፣ እስራትና እገታ ተፈጽሟል፡፡
👉 ጥፋተኞች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋል ካለባቸው በሕገ መንግሥቱና በፍትሕ ሥርዓቱ መሠረት ብቻ መሆን አለበት፡፡
👉በሕግ ማስከበሩ ሂደት ንጹሐን በጀምላ እንዳይጎዱና እያንዳንዱ እርምጃ በማስረጃ መመስረቱን ለማረጋገጥና የተፈጠሩ ችግሮች ካሉ ማብራሪያ ይሰጥ፡፡
👉ሀገር ለማፍረስ የተነሳውን የሽብር ቡድን ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የመከተውን አሁንም በምሽግ የሚገኘውን ፋኖንና የፋኖ አባላትን ማፈንና ማሳደድ አለ የሚል ቅሬታ ስላለ ማብራሪያ ቢሰጥ፡፡
👉ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የጋዜጠኝነት ነጻነት ግድ ይላል፣ በዚህ ወቅት ግን ጋዜጠኞች እየታሠሩ ነው፣ ጋዜጠኞች ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለፁ ብቻ የሚታሠሩ ከሆነ ከለውጥ በፊት ወደነበረው አፋኝ ስርዓት አይመልስም ወይ፡፡
👉በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የሕዳሴ ግድብ አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ ነው ያለው፡፡
👉የሌሎች ፕሮጄክቶችስ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በመንግሥት በኩል የተቀመጡ አቅጣጫዎች ምን ይመስላሉ፡፡
👉የኢትዮጵያ ሕዝብ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በብሔር የተጋመደ ነው፡፡ እሴቶቻችን አብረን እንድንኖር መሠረት የኾኑን ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን በሃይማኖት ሽፋን የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ የሃይማኖት ተቋማት ተቃጥለዋል፣ ሕዝቡም በዚህ ድርጊት እየተማረረ ነው፡፡

👉የጽንፈኝነት ችግር ሀገርን እንደ ሀገር ያጸኑ እሴቶችን በመጉዳት የሀገራችንን ሕዝቦች ለከፋ ጉዳት እየዳረገ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነታችንን በማዳከም ለውጭ ጠላት ተጋላጭ እንድንኾን ያደርገናል፡፡
👉የጽንፈኝነት ችግር በሂደት ሀገራችንን የሚያሳጣ በመኾኑ ችግሩን ለመቅረፍና የጽንፈኝነትን አካሄድ ለመመለስ የመንግሥት አቅጣጫ ምንድን ነው?
👉 በአሸባሪው ቡድን አሁንም የዋግኸምራ፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር፣ የአፋር ሕዝብ አሁንም ሰላም አላገኘም፣ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ቀጣናውን ሰላም በማድረግ ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ፣ የሰበዓዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ዕቅድ ካለ ቢብራራ?
👉ከትግራይ ክልል እየተፈናቀሉ ወደ አማራ ክልል ለሚገቡ ዜጎችስ የታሰበው ምንድን ነው?
👉የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር መንግሥት ምን እየሠራ ነው? የዘይት የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ማስተካከያ አድርገናል ቢባልም አሁንም እየጨመረ ነው፤ የማስፈጸም ችግር አለ ለምን አይስተካከልም?
👉ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እርምጃ ተወስዷል ቢባልም የኑሮ ውድነቱ ተባብሷል፡፡ መንግሥት ምን እየሠራ ነው?
👉ጽንፈኛ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞችን መንግሥት ለመቆጣጠር ምን አስቧል?
በታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበክረምቱ የዝናብ ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ጎርፍ እና መጥለቅለቅ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በብሔራዊ ሚቲዎሮሎጅ ኤጀንሲ የምዕራብ አማራ ሚቲዎሮሎጅ አገልግሎት ማእከል አስታወቀ፡፡
Next articleበኢትዮጵያ አየር መንገድና በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡