በክረምቱ የዝናብ ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ጎርፍ እና መጥለቅለቅ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በብሔራዊ ሚቲዎሮሎጅ ኤጀንሲ የምዕራብ አማራ ሚቲዎሮሎጅ አገልግሎት ማእከል አስታወቀ፡፡

177

አርሶ አደሮች የእርሻ ሥራቸውን ሲያከናውኑ የሚሠጠውን የአየር ሁኔታ ትንበያ መሠረት ማድረግ እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በብሔራዊ ሚቲዎሮሎጅ ኤጀንሲ የምዕራብ አማራ ሚቲዎሮሎጅ አገልግሎት ማእከል ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሲሳይ ቀለሙ የ2014 ዓ.ም የክረምት የዝናብ አጀማመር እንደሚዘገይ እና ዘግይቶ ሊወጣ እንደሚችል ትንበያው እንደሚያመላክት ነግረውናል፡፡ የክረምቱ ዝናብ በሰኔ ወር እንደሚጀምር የገለጹት ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ ሥርጭቱ በጀመረበት ልክ የማይጨርስ እና ደረቅ የሚኾንበት ሁኔታ መኖሩን በትንበያው መገለጹን ጠቅሰዋል፡፡
ሐምሌ እና ነሐሴ ከሚጠበቀው በላይ ዝናብ እንደሚኖር ትንበያው ማካተቱንም ጠቁመዋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ጎርፍ እና መጥለቅለቅ ሊከሠት ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
አቶ ሲሳይ አርሶ አደሮች ሣይንሳዊ ትንበያውን መሠረት በማድረግ የእርሻ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በጎርፍ የሚከሰትን ችግር ለመቀነስ ተጋላጭ የኾኑ አካባቢዎች ብቻ ሳይኾኑ ሁሉም አካባቢዎች ቀድመው መዘጋጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleኢትዮጵያና ጣልያን ለተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚውል የ22 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
Next articleየምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ሃሳቦችና ጥያቄዎች።