
ሰኔ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያና ጣልያን ለተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚውል የ22 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴና የጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ተፈራርመዋል።
ብድሩ የቡሬ፣ ቡልቡላ፣ ይርጋለምና ባአከር የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ማጠናከሪያና በፓርኮቹ ዙሪያ ለሚቋቋሙ የገጠር ሽግግር ማእከላት ግንባታ የሚውል ነው።
የብድር ስምምነቱ ኢትዮጵያና ጣልያን ያላቸውን ኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናክር መኾኑን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሺዴ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ በበኩላቸው ስምምነቱ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/