በአሜሪካ ቨርጂኒያ የምትኖረው የ15 ዓመቷ ታዳጊ ኢትዮጵያዊት በደብረ ብርሃን መጠለያ ለተጠለሉ ሴቶች ድጋፍ አደረገች፡፡

187

ደብረ ብርሃን: ሰኔ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ15 ዓመቷ ታዳጊ ቤተልሔም አስፋው በደብረ ብርሃን የመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጋለች፡፡
በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የምትኖረው የ11ኛ ክፍል ተማሪዋ በደብረ ብርሃን ከተማ በመጠለያ ጣቢያ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች 300 ሺህ ብር ማሰባሰብ ችላለች።
ታዳጊዋ ከአሰባሰበችው ገንዘብ 156 ሺህ ብር ወጭ በማድረግ ለሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጋለች። ቀሪው ገንዘብ በዘጌ ለሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚውል ነው የገለጸችው።
በቀጣይ ድጋፍ ለማድረግም ታዳጊዋ ቃል ገብታለች።

ድጋፍ የተደረገላቸው ሴቶች የሚቸግራቸውን በመለየት ድጋፍ ስለተደረገላቸው አመስግነዋል።
ድጋፉን ያስተባበረው ይፋት የልማት ማኅበር እንደኾነም ተገልጿል።
ዘጋቢ፡- ብርቱካን ማሞ – ከደብረ ብርሃን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአማራ ባንክ ሰኔ 11 ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።
Next article“የማያርሱ ገበሬዎች፣ ማረስ ማፈስ ናፋቂዎች”