አማራ ባንክ ሰኔ 11 ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።

580

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባንኩ የምረቃ ዕለትም 70 የተሟሉ ቅርጫፎች የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ይኾናል ተብሏል።
እሰከ ሰኔ 30 ባሉት ቀናቶች ባንኩ ቅርንጫፎቹን ከ100 በላይ የሚያሳድግ መኾኑንም ገልጿል።
የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ እንዳሉት ባንኩ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የተከፈተ ነው፤ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ የተጀመረ ባንክ ነው ብለዋል።
ባንኩ የሕዝብ ባንክ መኾኑን አንስተው እሰካሁን በብሔራዊ ባንክ ደንብ መሠረት የአክሲዮን ሸያጭ መከናወኑን አንስተዉ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች አክሲዮኖች ተሽጠዋል ብለዋል።
የካቲት 2/2014 ዓ.ም ዋና እና ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎችን ማስመረጡንም አንስተዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸዉ እስከ ሰኔ 30 አጠቃላይ 100 ቅርጫፎች ሥራ እንደሚጀምሩ ጠቅሰዉ ሰኔ 11 ላይ በመክፈቻዉ 70 ቅርጫፎች ሥራ ይጀምራሉ ብለዋል።
የሠራተኛ እና የሥራ ቁሳቁስ ግብዓት የማሟላት ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት።
ዋና መሪ ቃሉን “ከባንክ ባሻገር “ብሎ የጀመረዉ አማራ ባንክ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን በሥራዎቹ እንደሚወጣ አስታውቋል።
እስከ ሰኔ 11 ባሉት ቀኖችም ባንኩ የፓናል ዉይይት፣ የደም ልገሳ እና ሌሎችም መርኃግብሮች እንደሚኖሩት አመላክቷል።
ባንኩ የማኅበራዊ አገልግሎቱን ለመወጣት እንዲያስችለው ሥራ በሚጀምርበት ሰኔ 11 ቀን ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ የአምበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎችን ወጭ መሸፈኑን አስታውቀዋል።
ተጠቃሚዎችም በዕለቱም ያለምንም ክፍያ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም አስታውቋል።
ባንኩ ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል በመያዝ ሥራውን የጀመረ ሲኾን እስካሁንም ከ4 ቢሊየን ብር በላይ በሥራ ላይ ማዋሉን ባንኩ አስታዉቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ እና የዳኞች አሥተዳደር ጉባኤ ረቂቅ አዋጆችን በተመለከተ ምክክር እያደረገ ነው።
Next articleበአሜሪካ ቨርጂኒያ የምትኖረው የ15 ዓመቷ ታዳጊ ኢትዮጵያዊት በደብረ ብርሃን መጠለያ ለተጠለሉ ሴቶች ድጋፍ አደረገች፡፡