
ጎንደር: ሰኔ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ እና የዳኞች አሥተዳደር ጉባኤ ረቂቅ አዋጆችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጎንደር ከተማ ምክክር እያደረገ ነው።
በመድረኩ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አብዬ ካሳሁንን ጨምሮ የመንግሥት ሦስቱ አካላት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
የክልሉ ፍርድ ቤቶች እና ዳኞች የዳኝነት ሥራን ከውጫዊም ኾነ ውስጣዊ ተጽዕኖ ነጻ ኾነው በገለልተኝነት እና በተጠያቂነት ማከናወን እንዲችሉ የክልሉን ፍርድ ቤቶች የዳኞች አሥተዳደር ጉባዔ እንደገና ማደራጀት እና ማጠናከር አስፈልጓል ነው የተባለው።
በመድረኩም የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አሥተዳደር ጉባዔ ማቋቋሚያ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ይደረግበታል።
የክልሉ ፍርድ ቤቶች እና በየትኛውም እርከን የሚገኙ ዳኞች የሚሰጡት የፍትሕ አገልግሎት ግልጽ፣ የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር፣ የዳኝነት ነጻነት እና ተጠያቂነትን ሚዛናዊ በኾነ መልኩ የሚያረጋግጥ፣ የፍትሕ ፈላጊውን ሕዝብ እርካታ የሚያስገኝ እና አመኔታ ከፍ ያለ እንዲኾን ተቋማዊ አሠራሩን እንደገና ማጠናከር ያለመ መድረክ ነው።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ – ከጎንደር
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/