በኢትዮጵያ የሽብርተኝነት አደጋን ለመከላከል ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ የማሳደግ ተግባር በመከናወን ላይ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል ተመሥገን ጥሩነህ ገለጹ።

138

ሰኔ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ሽብርተኝነትን በመከላከል የጋራ ቤታችን የኾነችውን ኢትዮጵያ በጋራ እንጠብቃለን!” በሚል መሪ ሐሳብ ሀገር አቀፍ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል ተመሥገን ጥሩነህ፤ ሽብርተኝነት ሀገርና ሕዝብን አደጋ ላይ የሚጥል ዓለም አቀፍ ስጋት በመኾኑ የመከላከል ተግባሩ ኹሉንም ይመለከታል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ላይ ሊቃጡ የነበሩ የሽብር ድርጊቶችን በማክሸፍና በመከላከል ሂደት የተሳካ ሥራ መከናወኑንም አስታውሰዋል። በዚህ ተግባር አጠቃላይ የሕዝቡና የጎረቤት ሀገሮች አቻ ተቋማት የነበራቸውን ሚና አድንቀው ቀጣይነት እንዲኖረውም ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ የሽብርተኝነት አደጋን ለመከላከል ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብሯን ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር ተግባራትን በማከናወን ላይ መኾኗንም ጠቅሰዋል።
ሽብርተኝነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ኾኖ የቀጠለ የጋራ ችግር በመኾኑ የጋራ መከላከልን ይጠይቃል ነው ያሉት።
ኢዜአ እንደዘገበው በውይይት መድረኩ ወቅታዊ የሽብርተኝነት ስጋቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የሕግ የበላይነት መከበር እና መልካም አሥተዳደር መስፈን ለአስተማማኝ ሰላም፣ ለግጭት አፈታት እና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ ናቸው” ዶክተር ዘውዱ እምሩ
Next articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Caamsaa 30/2014