
ሰኔ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በሁሉም የፀጥታ መዋቅር ቅንጅት የተወሰደው ህግን የማስከበር ዘመቻ ከፍተኛ ውጤቶች የተመዘገበበት መኾኑን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ በመግለጫው እንዳሉት፤ ይህን ተግባር በበላይነበት የሚመራው የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤትም የህግ ማስከበር ዘመቻው መልካም ውጤት የታየበት መኾኑን ገምግሟል፡፡
የተወሰዱት እርምጃዎች ለሕዝቡ እፎይታ የሰጡ እና መልካም ውጤቶች የታዩበት ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታዋ በተለያዩ ጊዜያት ከአማራ ክልል መንግስት የተሰጡ መግለጫዎችም ይህንን ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል በከባድ ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ አካላትን ለህግ ማቅረብ እና ህገ ወጥነትን የመቆጣጠር ስራ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡
ሰላም እና ደህንነት በማስከበር እና የሽብር ቡድኖችን ማንነት ለሕዝቡ ከማሳወቅ አንፃር መልካም ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/