
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው ላይ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአዲሱ የሶማለያ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሸህ ሙሃመድ በዓለ ሲመት መታደማቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የሚያጠናክርና ቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮችን በማጠናከር ወደ ፊት አብሮ ለመሥራት አንደሚጠቅም ተናግረዋል።
አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ተቋምት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ጋር ምክክር ማድረጋቸውን ገልፀዋል። አቶ ደመቀ በአፋር ክልል ተገኝተው ያለውን ሰብዓዊ ድጋፍ ተመልክተዋል ያሉት ቃል አቀባዩ ለአማራ እና ለአፋር ሕዝብ የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን አብራርተዋል።
በስዊዘርላንድ የሚገኙ ሁለት ድርጅቶች በአማራ እና በአፋር ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ የገንዘብ እርዳታ እያሰባሰቡ መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።
ዘጋቢ፦ አንዷለም መናን
መረጃዎቻችንን ስለሚከታተሉ እናመሰግናለን!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/