በአማራ ልዩ ኃይል የ28ኛ ደጀን ክፍለ ጦር በሕግ ማስከበርና በኅልውና ዘመቻ የላቀ አበርክቶ ለነበራቸው አባላትና የኅብረተሰብ ክፍሎች የማዕረግ እድገትና ዕውቅና ሰጠ።

364

ወልድያ: ሰኔ 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ልዩ ኀይል የ28ኛ ደጀን ክፍለ ጦር በሕግ ማስከበርና በኅልውና ዘመቻ የላቀ አበርክቶ ለነበራቸው የልዩ ኃይል አባላትና የኅብረተሰብ ክፍሎች የማዕረግ አሰጣጥና የዕውቅና መርኃግብር በወልድያ ከተማ አካሂዷል።
የአማራ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ዘለቀ ክፍሌ ከሀዲዎች በፈፀሙብን ወረራ በርካታ ግዳጆችን አሳልፈናል ብለዋል። “ባሳለፍናቸው ግዳጆችም በጀግንነት የጠላትን ህልም በማክሸፍ ዛሬ ላይ ደርሰናል” ነው ያሉት።
የዕውቅና መርኃግብሩ ሠራዊቱን በማበረታታት ለቀጣይ ግዳጅ ጉልህ ድርሻን ለማበርከት ታላሚ ያደረገ መኾኑን ረዳት ኮሚሽነር ዘለቀ ክፍሌ ጠቅሰዋል።


በመርኃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ ወልደማርያም “ኢትዮጵያን ለማዳን በጋራ ለምናደርገው ትግል የዛሬው ዕውቅና የትጋት ስንቃችሁ ነው” ብለዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የማዕረግ እድገት የተሰጣቸው የልዩ ኃይል አባላትም በተሰጣቸው ዕድገት መደሰታቸውን ገልጸዋል። ለቀጣይ ግዳጅም ብርታት እንደሚኾናቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ካሳሁን ኀይለሚካኤል -ከወልድያ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናከር ያላቸውን እምነት ገለጹ።