‟የገጠመንን ሀገራዊና ክልላዊ ችግር ለመፍታት ዴሞክራሲን መትከል የሚችል መሪ ያስፈልጋል” የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ።

186

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ለከፍተኛና መካከለኛ መሪዎች ከሰኔ 02 እስከ 07/2014 ዓ.ም ለሚሰጠው ስልጠና የመክፈቻ መድረክ አዘጋጅቷል።

ለመሪዎቹ የሚሰጠው ስልጣና “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ፣ አዲስ ሀገራዊ እመርታ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ የተዘጋጀ ነው።

በስልጠና መክፈቻ መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ “የገጠመንን ሀገራዊና ክልላዊ ችግር ለመፍታት ዴሞክራሴን መትከል የሚችል መሪ ያስፈልጋል” ብለዋል። የስልጠናው ዓላማም በብልጽግና አባላት ውስጥ እኩል አስተሳሰብ ፣ ቁርጠኝነት እና ብቃት ያለው መሪ እንዲፈጠር ታልሞ መዘጋጀቱን ነው ያስገነዘቡት።

የለውጥ አመራሩ የፓርቲውን ርዕይ የተረዳና የሚያሳካ መኾን አለበት፤ ከስልጠናው ማግስት መሪዎች የሕግ የበላይነት የሚያሰፍኑ፣ ክልሉ ላይ ያሉ የቤት ሥራዎችን የሚወጡ እንዲኾኖ ይጠበቃል ነው የተባለው።

ፓርቲው በምርጫ የተረከበውን ኀላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ተግባር መፈጸም ይጠበቅበታል ያሉት አቶ ግርማ ለ5 ቀናት የሚቆየው ስልጠናና ግምገማ ቁልፍ ተግባራት የሚተላለፉበት ፣ ሕዝቡን አሳትፎ ክልሉንና አካባቢውን በልማት መለወጥ የሚችል መሪ መፍጠር የሚያስችል ይኾናል ብለዋል።

‟በዚህ ስልጠና የገጠመንን ሀገራዊና ክልላዊ ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሔ ሃሳቦች የሚተላለፉበት እና የዴሞክራሴ ግንባታ ሥራ ቁልፍ ተግባር የሚከውኑበት ነው” ብለዋል።

አቶ ግርማ ‟የገጠመንን ሀገራዊና ክልላዊ ችግር ለመፍታት ዴሞክራሲን መትከል የሚችል አመራር ያስፈልጋል” ነው ያሉት፡፡ ስልጠናው ይህን ሀገር ወደ አዲስ ፖለቲካል አስተሳሰብና አዲስ ዕይታ የሚለውጥ እንዲኾን እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

ጠንካራ መሪ ለመፍጠር ታስቦ በተዘጋጀው ስትራቴጅክ ስልጠና ከ2ሺህ 80 በላይ መሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል።

ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleኢዜማ ለቀጣይ ዓመታት ፓርቲዉን የሚመሩትን እጩዎች ይፋ አደረገ።
Next articleበወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ