ኢዜማ ለቀጣይ ዓመታት ፓርቲዉን የሚመሩትን እጩዎች ይፋ አደረገ።

255

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ( ኢዜማ ) በቀጣይ ዓመታት ፓርቲዉን ለመምራት የሚወዳደሩት እጩዎች የሚያደርጉትን የምርጫ ቅስቀሳ በማስመልከት መግለጫ ሰቷል።
የኢዜማ የምርጫ ኮሚቴ ጸሀፊ ወይዘሮ ቅድስት ግርማ የእጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ከዛሬ ጀምሮ እሰከ ሰኔ 24 ይከናወናል ብለዋል።
ተመራጮች የፓርቲዉን ህግ እና ደንብ ማክበር ይኖርባቸዋል ሲሉ አንስተዋል።
ምርጫዉን ፍትሀዊ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን የምርጫ ኮሚቴዉ አስታዉቋል።

ማንኛዉም እጩ እነዚህን ግዴታዎች ማሟላት እንዳለበት ኮሚቴዉ አስታዉቋል፦
▶️ የሌሎችን እጩዎች ክብር መንካት የተከለከለ መኾኑን፣
▶️ የፓርቲዉን የስነ ምግባር ደንቦችን ማክበር እንደሚገባ፣
▶️ ከቡድንተኝነት መጽዳት በተለይም በመገናኛ ቡዙኃን በሚሰጡ ሀሳቦች ላይ በጥንቃቄ ማቅረብ እንደሚገባ ተገልጿል።
ኮሚቴዉ ይህ ምርጫ ትልቅ ተቋም የሚገነባበት መኾኑን በማወቅ ፍትሀዊ ስራዎችን እያከናወነ መኾኑን አንስቷል።
ፓርቲዊዉ በማህበራዊ ድረገጹ ላይ ላይ የእጩዎችን ዝርዝር ማስቀመጡን አስታዉቋል።

ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉእሽ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር ከ500 ሚሊዮን በላይ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ተዘጋጅተዋል።
Next article‟የገጠመንን ሀገራዊና ክልላዊ ችግር ለመፍታት ዴሞክራሲን መትከል የሚችል መሪ ያስፈልጋል” የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ።