በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር ከ500 ሚሊዮን በላይ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ተዘጋጅተዋል።

273

ሰኔ 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር ከ500 ሚሊዮን በላይ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መኾናቸውን የብሔራዊ አረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር ቴክኒክ ኮሚቴ ገለጸ።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሐሳብ አመንጭነት “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ መልዕክት ላለፉት ሦስት ዓመታት ተካሂዷል።
በዚህም በየዓመቱ 92 ሺህ ሄክታር የነበረውን የደን ውድመት መጠን ወደ 32 ሺህ ሄክታር ዝቅ ማድረግ ተችሏል።
የዘንድሮው አራተኛ ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር በያዝነው ወር አጋማሽ ላይ ይጀመራል።

የብሔራዊ አረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ ዶክተር አደፍርስ ወርቁ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ መርኃግብሩ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይኾን የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ ያስችላል። ይህም ዘላቂ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ መኾኑን አንስተዋል፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች ተመናምኖ የነበረው የተፈጥሮ ኃብት እንዲያገግም መደረጉን ገልጸዋል።
መርኃ ግብሩ የተፈጥሮ ኃብት እንክብካቤ እንደ አንድ አጀንዳ ኾኖ በሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ልዩ ትኩረት የተሰጠው መኾኑንም ጠቁመዋል።
አሁን በመላው ሀገሪቱ ያሉት የችግኝ ጣቢያዎችም 120 ሺህ መድረሳቸውን ገልጸው ይህም በሥራ ፈጠራ ረገድ በርካታ የሥራ እድልን መፍጠር የቻለ ነው ብለዋል።
በዘንድሮው በአራተኛው ዙር የአረንዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ከ500 ሚሊዮን በላይ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ማንጎና አፕል በዋናነት ለምግብነት ከሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች በዘንድሮው የችግኝ ተከላ የሚተከሉ መኾናቸውን ጠቁመዋል። እነዚህ ችግኞች በቀጣዮቹ ዓመታት ራስን በምግብ ከመቻል ባለፈ ለገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እንደሚያሳድጉ ገልጸዋል።
ወቅቱ ለችግኝ ተከላ ምቹ መኾኑን የገለጹት ዶክተር አደፍርስ ኅብረተሰቡ ከዚህ ቀደም ያሳየውን መነቃቃት እንዲደግመው ጠይቀዋል።
ችግኞች ከተተከሉ በኋላ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳቡት።

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ከ6 ነጥብ 3 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተዘጋጅተዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ።
Next articleኢዜማ ለቀጣይ ዓመታት ፓርቲዉን የሚመሩትን እጩዎች ይፋ አደረገ።