
ግንቦት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ።
ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ በአንድ ግለሰብ ቤት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ 23 የሞርተር ተተኳሽ (ቅንቡላ) ተከዝኖ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የተገኘው የሞርተር ተተኳሽ አሸባሪው ሕወሀት ቡድን ከአካባቢው ሸሽቶ ሲሄድ ጥሎት የሄደው ሊሆን እንደሚችልም የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያስታወቀው።
ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብም በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/