
ግንቦት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዋግኽምራ ሀገረ ስብከት ከሰባት ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ብርድ ልብስና ፍራሾችን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የዋግኽምራና የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስ እንዳሉት ሀገረ ስብከቱ በሀገሪቱ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚኾን የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፎችን እያቀረበ ነው። በዚህም በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር እስካሁን ድረስ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የሰብዓዊ ድጋፎችን ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቅረባቸውን ነው ያስታወሱት።
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የተፈናቃይ ቁጥር መጨመር ተከትሎ በተደረገው ጥሪ መሰረት በውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የወገን አለኝታነታቸውን አሳይተዋል ብለዋል።
በጥሪው መሠረት ከሰባት ሚሊየን 400 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው 3 ሺህ 421 ብርድ ልብስ፣ 1 ሺህ 862 ፍራሽ፣ 800 ኩንታል ዱቄት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን ብፅዕነታቸው ገልጸዋል።
በውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላደረጉት ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን መሪ ወይዘሮ ዝናሽ ወርቁ ሀገረስብከቱ ያደረገው ድጋፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን ችግር የሚያቃልል ነው ብለዋል።
ሀገረ ስብከቱ ያደረገው ድጋፍ የተፈናቀሉ ወገኖች ያሉባቸውን ችግር የለየ መኾኑን ወይዘሮ ዝናሽ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ሀገረ ስብከቱ ላደረገው የሰብዓዊ ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል።
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በአሁኑ ወቅት ከ89 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ የተገለጸ ሲኾን በጎ ፈቃደኛ ተቋማትና ግለሰቦች ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደርጉትን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/