
ግንቦት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፖሊስ ተቋማትን የማዘመንና የማጠናከር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታወቁ።
“በመስዋዕትነታችን የሀገራችን ሰላምና አንድነት ይረጋገጣል” በሚልመሪ ሃሳብ ለፀጥታ አካላት የምሥጋናና ዕውቅና አሠጣጥ ፕሮግራም በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር) በሽልማቱ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ 100 ሚሊዮን ህዝብን የሚመጥን ዘመናዊና ጠንካራ የፖሊስ ተቋማት ያስፈልጋሉ፤ በፌዴራል ፖሊስ ውስጥም ይህንን የሚመጥን መሠል ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ብለዋል።
አሁን የተጀመረውና በዛሬው እለት የተመለከትነው የፌዴራል ፖሊሰ ተቋማትን የማዘመንና የማጠናከር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የኢትዮጵያ ፖሊስ በጎችን ከተኩላዎች ለመጠበቅ 24 ሰአት የሚሰራ ሃይል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብዙ ተኩላዎች ሲጮሁ ይሰማል፤ የጩኸቱ ትርጉም በጎችን እንደፈለግነው እንብላ ተዉን ነው፤ ፖሊሶች ከተኩላዎች ምስጋና አይገኝምና ስራችሁን አጠናክራችሁ እንደትቀጥሉ ሲሉም አሳስበዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ ሃይሎች ይፈርሳሉ ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፤ ፌዴራል ፖሊስ ለመላው ሕዝብ ጋሻ ለመሆን የሚያስችለውን ቅም እየገነባ ነው ብለዋል።
የፌደራል ፖሊስ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) የቅርብ ክትትል ተቋሙ ዘመናዊና ቀዳሚ የሚያደርገውን መሣሪያዎች ታጥቋል ብለዋል።
የዛሬው እውቅናና ምስጋና መርኃ ግብርም በየደረጃው ችንደሚቀጥል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።
በዛሬ የምስጋናና እውቅና መርሀ ግብር ላይ ጀግንነት ለፈፀሙና የላቀ የሥራ ውጤት ላስመዘገቡ አመራርና አባላት ምሥጋናና ዕውቅና ተሰጥቷል።
በመርሀ ግበሩ ላይም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ሚኒስትሮች፣ የውጭ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ ቀዳማዊት እምቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የፖሊስ አባላት ገኝተዋል።
በመርኃግብሩ ወታደራዊ ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን፤ ፖሊስ በአሁኑ ሰአት የደረሰበትን ደረጃ ያሳዩ ሁነቶች ለእይታ ቀርብዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/