በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ለኮምቦልቻ ሆስፒታል የ9 ሚሊየን ብር የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

135

ግንቦት 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ነዋሪነታቸውን በካናዳ ያደረጉት ኢትዮጵያዊ ለኮምቦልቻ አጠቃላይ ሆስፒታል 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉን ያደረጉት አቶ ከበደ ሃይለማሪያም የህክምና ቁሳቁሱ ከቤተሰቦቻቸውና ከጎደኞቻቸው ጋር በመሆን ያሰባሰቡት ነው፡፡

አቶ ከበደ ከዚህ በፊት አንድ ኮንቴነር የህክምና ቁሳቁስ ለሆስፒታሉ ድጋፍ ቢያደርጉም አሸባሪው ቡድን እንዳወደመውና እንደዘረፍው ገልጸው÷አሁን ላይ ሆስፒታሉ ከደረሰበት ውድመት እንዲያገግም ተጨማሪ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር ሆስፒታሉ በሽብር ቡድኑ ህወሓት ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ውድመት ቢደርስበትም፤ በመንግስትና በበጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍም በሆስፒታሉ ይስተዋል የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት በእጅጉ እንደሚቀርፍ ነው የገለጹት፡፡

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንደሰን ልሳነ ወርቅ÷ አሸባሪው ህወሓት በከተማዋ በሚገኙ የመንግስት ተቋማትና ትልልቅ ፍብሪካዎች ላይ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት ማድረሱን አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይም ተቋማቱ እየተደረገላቸው ባለው ድጋፍ ከደረሰባቸው ጉዳት በማገገም ወደ ስራ እየተመለሱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአውስትራሊያው ፎርትስኪው ፊውቸር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ አረንጓዴ ሃይድሮጂንና አሞኒያ በማምረት ሊሰማራ ነው።
Next article“የፖሊስ ተቋማትን የማዘመንና የማጠናከር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)