የአውስትራሊያው ፎርትስኪው ፊውቸር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ አረንጓዴ ሃይድሮጂንና አሞኒያ በማምረት ሊሰማራ ነው።

84

አዲስ አበባ:ግንቦት 26/2014 ዓ.ም(አሚኮ) የአውስትራሊያ የኢንቨስትመንት ተቋም የኾነው ፎርትስኪው ፊውቸር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ አረንጓዴ ሃይድሮጂንና አሞኒያ ምርት ላይ በመሰማራት ለታዳሽ ኀይል ለማዋል እንደሚሠራ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡
የገንዘብ ሚኒሰትር አሕመድ ሽዴ የአውስትራሊያ ፎርትስኪው ፊውቸር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ምርት ሥራ ስኬታማ እንዲኾን መንግሥት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አሰታውቀዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን በማጎልበት፣ ከበካይ ጋዝ የጸዳ የኀይል ምንጭ በማቅረብ፣ ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር፣ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ታዳሽ ኀይል በማምረት ለሀገሪቱ ልማትና እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል፡፡
እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ2020 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአውስትራሊያው ፎርትስኪው ፊውቸር ኢንዱስትሪ ጋር የአረንጓዴ ሃይድሮጂን እና አሞኒያ ፕሮጀክት ለማሰጀመር ውይይት ሲያደረግ እንደቆየ ሚኒስትሩ አሰታውሰዋል።
ኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ማእከል በማድረግ በሀገር ውስጥም ኾነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የኃይል አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ እንደሚሠራም ተናግረዋል።
የፎርትስኪው ፊውቸር ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጁሊ ሹትልዎርዝ እንደተናገሩት ተቋማቸው አረንጓዴ ሃይድሮጂንና አሞኒያ በማምረት የካርቦን ልቀትን ዜሮ በማድረስ መቶ በመቶ ታዳሽ ኃይልን ጥቅም ላይ ያውላል፡፡
ኢትዮጵያ በጂኦተርማል፣ በንፋስ፣ በውኃ እና በፀሐይ ኃይል ያላት እምቅ ሀብት ምርጫችን አድርጓታል ሲሉ መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
አረንጓዴ ሃይድሮጂንና አሞኒያ ለማዳበሪያ፣ ለሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ለከባድ ተሽከርካሪዎች፣ ለባቡርና ለመርከብ ትራንስፖርት ኀይል ምንጭነት የሚያገልግል ከበካይ ጋዝ የጸዳ የኀይል ምንጭ ናቸው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2015 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ።
Next articleበካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ለኮምቦልቻ ሆስፒታል የ9 ሚሊየን ብር የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።