በበጀት ዓመቱ ይሠራሉ ተብለው የተያዙ መሰረተ ልማቶች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

139

ፍኖተሰላም: ግንቦት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን በበጀት ዓመቱ 3 መቶ 68 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ 124 አዳዲስ እና 9 ነባር ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑ ተመላክቷል።
የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ መንገድ፣ የዲች ቦይ ግንባታ፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ ማስፋፋት፣ የመብራት መስመር ዝርጋታ፣ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታና ሌሎች መሰረተ ልማቶች በዞኑ በተለያዩ ከተሞች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡
በመራዊ ከተማ አስተዳደር 50 ሚሊዮን በሚጠጋ በጀት 21 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመከናወን ላይ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጋሻው እንየው ተናግረዋል፡፡ 3 ነጥብ 2 ኪ.ሜ የጎርፍ ማፋሰሻ ዲች ቦይ፣ 800 ሜትር የጌጠኛ መንገድ፣ የመብራት መስመር ዝርጋታ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታና መሠል መሠረተ ልማቶች በመሠራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
እየተገነቡ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ መሰረተ ልማቶቹን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነውም ብለዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ 93 ሚሊዮን ብር በሚሆን በጀት 43 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመከናወን ላይ ናቸው ያሉት ደግሞ የቡሬ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም አወቀ ናቸው፡፡
ከባለሙያ ክትትል ባሻገር ከማኅበረሰቡ በተቋቋመ ግብር ኃይል የመሰረተ ልማቶችን ጥራት ለማስጠበቅ እየተሠራ ነው ያሉት አቶ ዘላለም ፕሮጀክቶችን እስከ ሰኔ 30 ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነውም ብለዋል፡፡
በከተሞች በሚከናወኑ መሰረተ ልማቶች በርካታ ወጣቶች የሥራ እድል ተጠቃሚዎች ሆነዋል፡፡ከነዚህ መካከል ወጣት የዝና መንግሥቱና ዓለሙ ሆድሞኝ በዲች ቦይ ስራ እና በጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ የተሰማሩ ሲሆን መሰረተ ልማቶችን በጥራት ገንብተው ለማስረከብ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በዞኑ 3 መቶ 68 ሚሊዮን ብር በሚሆን በጀት 124 የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኀላፊ አቶ ዓላምር ተሻለ ናቸው፡፡
በወቅታዊ ሀገራዊ ችግሮችና ሌሎች ምክንያቶች ፕሮጀክቶች ዘግይተው ቢጀመሩም አሁን ላይ የ90 ቀናት እቅድ በማቀድ እስከ ሰኔ 30 ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው ያሉት መምሪያ ኀላፊው ከመሰረተ ልማት ግንባታ ባሻገር የከተሞች ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችንም ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራት ላይ ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ :– ዘመኑ ይርጋ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢንዱስትሪ ፓርኮችን መሰረተ ልማት በማሟላት ለባለ ሃብቶች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ነው።
Next articleየሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2015 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ።