ዓለም ስለኢትዮጵያ ያለው አረዳድ ትርክቱ ሊቀየር እንደሚገባ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ገለጹ።

249

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሁን ላይ በሀገሪቱ የሚሰሩት የልማት ስራዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ዓለም እየተረዳበት ያለው ኹኔታ ትርክቱ ሊቀየር እንደሚገባ የሚያመላክት ነው ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ተናገሩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በባሌ ዞን፣ ሲናና ወረዳ 42 ሺህ 901 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር እየለማ ያለን የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩት ኦባሳንጆ በሰጡት አስተያየት፥ “አሁን በሀገሪቱ የግብርና ዘርፍ እየተሰራ ያለው ልማት ኢትዮጵያ ለህዝቧ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ጭምር ለውጥ ማምጣት የምትችል ሀገር መሆኗን የሚያሳይ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ያጋጠመውን ጦርነት ብቻ ሳይሆን እየተሰሩ ያሉ አበረታች የግብርና እንቅስቃሴዎችን መመልከት ችያለሁ ያሉት ልዩ መልዕክተኛው፤ መሬት ላይ ያለውን ይህን እውነት ዓለም እንዲገነዘብ በተደጋጋሚ ማስረዳት እና ማሳየት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ዓለም ስለጦርነቱ መዘገብ ብቻ ሳይሆን ለሰላም ዋስትና የሚሆኑ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጭምር በመመልከት ኢትዮጵያን በዚህ ደረጃ ሊረዳት ይገባልም ብለዋል የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት።

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን በበኩላቸው በአፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች የተሰሩ የግብርና ልማት ስራዎችን መጎብኘታቸውን አንስተው በኢትዮጵያ የተሰራው የግብርና ልማት ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የያዘቸውን መሰል የልማት እንቅስቃሴ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና ስለሚኖረው የዓለም ባንክ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ኃላፊው። ዘገባው የኢቢሲ ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Caamsaa 15/2014
Next articleየኢንዱስትሪ ፓርኮችን መሰረተ ልማት በማሟላት ለባለ ሃብቶች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ነው።