
ደባርቅ: ግንቦት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ ድል ይብዛ ከተማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ሕክምና ሲከታተሉ ያገኘናቸው የወረዳው ነዋሪዎች የጤና መድኅን አባል በመኾናቸው ለሕክምና የተጋነነ ወጭ ከማውጣት እንደታደጋቸው ገልጸዋል።
በጤና ጣቢያው ባለቤታቸውን ለማሳከም ወረፋ እየጠበቁ ያገኘናቸው አቶ አንዷለም ጥሩነህ በ2014 ዓ.ም ለ 10 የቤተሰብ አባላት 480 ብር ከፍለው ቤተሰቡ የጤና እክል ሲያጋጥመው ወደ ጤና ጣቢያው እየመጡ ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እንደሚያገኙ ተናግረዋል።
አርሶአደሩ አክለውም “የጤና መድኅን አባል ባንኾን ኖሮ ለዓመት ለአስሩ ቤተሰብ የከፈልኩት 480 ብር ለአንድ ጊዜ ሕክምና አይበቃም ነበር” ሲሉ የኅብረተሰብ ጤና መድኅን አባል የመኾንን ጠቀሜታ ያስረዳሉ።
በባለቤታቸው ተደግፈው ወደ ጤና ጣቢያው የመጡት ታካሚ ወይዘሮ ጥሩ አዘዘ በበኩላቸው “የጤና መድኅን አባል ኾነን አንድ ጊዜ በከፈልነው ብር የጤና እክል ሲያጋጥመን ያለምንም ወጭ እየታከምን ጤናችንን እየጠበቅን ነው” ብለዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ሐብቴ አስማረ በወረዳው ከ 97 ሺህ በላይ ሕዝብ እንደሚኖር ተናግረዋል። ከዚህ መካከልም ከ90 በመቶ በላይ የሚኾነውን ሕዝብ የኅብረተሰብ ጤና መድኅንን ጠቀሜታ ተገንዝቦ አባል እንዲኾን ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
የበየዳ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ጤና መድኅን የሃብት አሰባሰብና አጋርነት ቡድን መሪ አቶ አማረ ክንዴ በጤና መድኅን የማኅበረሰቡ እርካታ ለማስቀጠልና የቀሩትን አባል ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- አድኖ ማርቆስ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/