
ጎንደር: ግንቦት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አካባቢያዊ ተደራሽነቱን ለማስፋት ስድስት የኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያዎችን ከፍቶ ወደ ሥራ ገብቷል። ከነዚህም ውስጥ አማራ ኤፍ ኤም ጎንደር 105.1 አንዱ ነው። ይህ ጣቢያ ዛሬ የአንደኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አስቻለ አየሁዓለም “የአማራ ኤፍ ኤም ጎንደር 105.1 ተደራሽነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ ነው” ብለዋል፡፡
የአሚኮ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ሞገስ በበኩላቸው አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አማራ ኤፍ ኤም ጎንደር 105.1 በጥራት ተደራሽ እንዲኾን እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ሕዝቡ እና የመንግሥት መዋቅሩ ተቋሙ የራሱ መኾኑን አውቆ ሊጠቀምበት እና ሊደግፈው ይገባል ነው ያሉት፡፡
በበዓሉ ላይ የተገኙት የምዕራብ ጎንደር ዞን መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ኀላፊ አቶ ፈንታሁን ቢኾነኝ ከጣቢያው ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን ብለዋል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ኀላፊ አቶ ካሳሁን ንጉሤ ጣቢያዉ ከተመሠረተ ጀምሮ ለኅልውና ዘመቻው ላበረከተው አስተዋጽኦ ምሥጋና አቅርበዋል።
አማራ ኤፍ ኤም ጎንደር 105.1 አራት የቀጥታ ሥርጭቶችን ጨምሮ 18 ፕሮግራሞችን ቀርጾ ወደሥራ ገብቷል።
ዘጋቢ፡- አዲስ ዓለማየሁ-ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/