ባለሃብቶች በማዕድን ዘርፍ በመሰማራት ክልሉን እንዲያለሙ የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ጥሪ አቀረበ።

434

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ከባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባባር በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳርምድር እና በእናርጅ እናውጋ ወረዳዎች ላይ የሚገኙ ማዕድናት ክምችት እና ሥርጭታቸው ምን እንደሚመስል ጥናት አካሂዷል።

የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ኃይሌ አበበ በክልሉ 21 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ላይ የማዕድን ሃብት ላይ ጥናት መደረጉን ገልጸዋል። ኀላፊው በእነዚህ ጥናቶች በአምስት ዘርፍ የሚከፈሉ 35 ዓይነት ማዕድናት መኖራቸውን ጠቁመዋል። እስካሁን በዘርፉ በርካታ ጥናቶች የተካሄዱ ቢኾንም ወደ ሥራ የገቡ ባለሃብቶች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው ብለዋል።

አቶ ኃይሌ እንደገለጹት በርካታ ባለሃብቶች በዘርፉ ፍቃድ ወስደል፤ ኹለት የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ለማቋቋምም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

ባለሃብቶች በዘርፉ በመሰማራት ክልሉን እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል። አሁን የተለያዩ ጥናቶች መካሄዳቸውን ተከትሎ ባለሃብቶች ለማልማት ፍላጎት እያሳዩ መኾናቸውን ጠቅሰዋል። ሌሎች አካላትም በዘርፉ በኢንቨስትመንት ከመሠማራት በተጨማሪ ጥናት በማድረግ የክልሉን የማዕድን ጸጋ መለየት ተገቢ መኾኑን ገልጸዋል።

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሥነ ምድር ሳይንስ ትምህርት ቤት ዲን እና የጥናቱ አስተባባሪ ምንያህል ተፈሪ (ዶ.ር) በጥናቱ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚኾኑ ማዕድናት መገኘታቸውን ጠቁመዋል። በጥናቱ የተገኙ ማዕድናት መጠናቸውን እና ጥራታቸው ምን ያህል እንደኾነ ተጠቁሟል። ከተገኙ ማዕድናት መካከል ጅብሰም፣ ለሲሚንቶ ፋብሪካ ግብዓት የሚኾን ላይምስቶን እና ብረት በብዛት የተገኙ ናቸው። ለልዩ ልዩ ጌጣጌጥ መሥሪያ የሚውሉ ማዕድናት መገኘታቸውን ዶክተሩ ገልጸዋል።

ዶክተር ምንያህል እንዳሉት ቢሮው የጥናት ውጤቱን ይዞ ለባለሃብቶች በማስተዋወቅ አካባቢዎቹ የሚለሙበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት ብለዋል። በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሃብቶች ለብክነት እንዳይዳረጉ አቅዶ መሥራት ተገቢ መኾኑንም አስገንዝበዋል።

በአማራ ክልል በማዕድን ዘርፉ ሠፊ ጥናት መደረግ እንዳለበት የጠቆሙት ዶክተሩ ከማዕድን ቢሮ በተጨማሪ ሌሎች አካላትም ትኩረት ሠጥተው እንዲሠሩ ጠይቀዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሥነ ምድር ሳይንስ ትምህርት ቤት በቦረና፣ በእነብሴ ሳር ምድር፣ እናርጅ እናውጋ ወረዳዎች የሠራውን የጥናት ውጤት፣ የካርታ እና የሥነ ምድር ጥናት ውጤቶች ለማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ አስረክቧል።

ዘጋቢ:- ትርንጎ ይፍሩ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዜና መጽሔት ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
Next article“እንደ አንድ ልብ ምከር፣ እንደ አንድ ቃል ተናገርʺ