“አርሶ አደሮች ያለውን ግብዓት በአግባቡ እንዲጠቀሙ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች እና ኀላፊዎች በትኩረት መሥራት ይገባቸዋል” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

71

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በምርት ዘመኑ በቅድመ ዝግጅት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በቀጣይ የሚከናወኑ ሥራዎች ላይ ከክልልና ከዞን የሥራ ኀላፊዎች ጋር ወይይት አካሂዷል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በሰጡት የሥራ መመሪያ አርሶ አደሮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ልማት እንዲገቡ አሳስበዋል፡፡ አርሶ አደሮች ያለውን ግብዓት በአግባቡ እንዲጠቀሙ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች እና ኀላፊዎች በትኩረት መሥራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

አርሶ አደሮች ሀገር በቀል የአፈር ማዳበሪያ እና ሌሎች ግብዓቶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ርእሰ መሥተዳደሩ አሳስበዋል።

በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የክልሉ መንግሥት የእርሻ ትራክተሮች ማቅረቡን አንስተዋል። በቀጣይ ዓመት የትራክተር ሥርጭት እና ሜካናይዜሽን ሥራ በስፋት ተግባራዊ ይደረጋልም ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በ2014/15 የምርት ዘመን 143 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየሠራ መኾኑ በመድረኩ ተገልጿል።

ዝርዝር መረጃውን እናደርሳለን

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ ግንቦት 22/2014 ዓ.ም ዕትም
Next articleበ2013 ዓ.ም ክረምት ከተተከሉ ችግኞች ውስጥ 80 በመቶው መጽደቁን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡