ሠራዊቱ የሚሰጠውን ማንኛውንም ተልዕኮ በከፍተኛ ብቃት መፈጸም በሚችልበት የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የ8ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮለ አስታወቁ።

345

ግንቦት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሠራዊቱ የሚሰጠውን ማንኛውንም ተልዕኮ በከፍተኛ ብቃት መፈጸም በሚችልበት የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የ8ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮለ አስታውቀዋል።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የ8ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮለ ሀገር አደጋ ላይ በወደቀችበት ጊዜ የተመሠረተው 8ኛ ዕዝ በዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት በተደረጉ አውደውጊያዎች ከፍተኛ ተጋድሎና አስገራሚ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም የዕዙን የሠራዊት አመራርና አባላት በሥልጠና በማብቃትና በኹሉም ዘርፍ በሚባል ደረጃ ሙያዊና የአመራር ክህሎታቸውን በማሳደግ በሥነ-ልቦና፣ በአካል እና በትጥቅ ዝግጁነቱ የተረጋገጠ የጦር ክፍል መገንባት መቻሉን አረጋግጠዋል።

የዕዙ የሠራዊት አባላት ከሚሌ በመነሳት በካሳጊታ፣ በቡርቃ፣ በባቲ፣ በቆቦና በሌሎች የግዳጅ ስፍራዎች ከፍተኛ ተጋድሎ በመፈፀም ሀገርንና ወገንን ያኮራ ተግባር መፈጸማቸውን የጠቀሱት ዋና አዛዡ በቀጣይም የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አቅምና ብቃት ተላብሰው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የዕዙን የሠራዊት አባላት ወታደራዊ ብቃት ለማሳደግ በየዘርፉ በተደረገ የሥልጠና ሂደትም በተቋሙ ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍ መደረጉን የገለጹት ዋና አዛዡ የተፈጠሩ አቅሞችን በመጠቀም የሀገርን እና የሕዝብን ሰላም ማረጋገጥ የዕዙ ቀዳሚ ተግባር መኾኑን እንደገለጹ ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአማራ ክልል እየተካሄደ የሚገኘዉን የህግ ማስከበር ሥራ ዉጤታማ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
Next articleበኩር ጋዜጣ ግንቦት 22/2014 ዓ.ም ዕትም