
ደብረብርሃን: ግንቦት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረጻዲቅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ሃይማኖትና ብሔር ላይ ተወሽቀዉ የሚዳክሩ ኀይሎችን በህግ ጥላ ሥር ለማዋል ከህዝቡ ጋር በጋራ በመሆን እየተሠራ ነዉ ብለዋል።
ህዝቡ የሚያነሳቸዉን ዉስጣዊ ችግሮች ለመፍታት በተለያዩ መድረኮች ዉይይት መደረጉን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪዉ በፋኖ ስም በህገወጥ ድርጊት የተሰማሩ ቡድኖችን አደብ ለማስገዛት የዞኑ አስተዳደር በቁርጠኝነት እየሰራ ነዉ ብለዋል።
በማኅበራዊ ማዲያዎች የሚነዛዉ ትጥቅ ለማስፈታት የክልሉ መንግስት እየሰራ ነዉ የሚባለዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ ያሉት አቶ ታደሰ በህገወጥ ድርጊት ላይ የተሰማሩ ቡድኖች ከድርጊታቸዉ የማይማሩ ከሆነ መንግስት ህጋዊ ርምጃ ይወስዳል ብለዋል።
በዞኑ እየተካሄደ በለዉ ህግ የማስከበር ስራ 302 ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር ዉለዉ ጉዳያቸዉ እየታየ መሆኑንም ገልጸዋል።
የዞኑ ህዝብ የክልሉ መንግስት እያካሄደ ያለዉን የህግ ማስከበር ስራ ዉጤታማ ለማድረግ ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:–ሀብታሙ ዳኛቸዉ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/