
ደሴ: ግንቦት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር እየተካሄደ ባለው የሕግ ማስከበር ተግባር ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር የነዋሪውን እና የከተማውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የሕግ የበላይነትን ለማስፈን እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።
በሂደቱም ከመቶ ያላነሱ የሕዝቡን ሰላም ሲያናጉ፣ የሃይማኖት ግጭት ለማስነሳት ሲሞክሩ የነበሩ፣ በጠራራ ፀሐይ ዘረፋ ሲፈጽሙ የቆዩና በሕገወጥ መሳሪያ ዝውውር ላይ እጃቸው ያለባቸው ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መኾኑን የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ተናግረዋል።
የሕግ ማስከበር ሥራው ውጤታማ እንዲኾን የሕዝቡ ሚና ከፍተኛ ነበር ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው
ከንቲበው በቀጣይ የሕግ ማስከበር ሥራው የበለጠ ውጤታማ እንዲኾን ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- አሊ ይመር-ከደሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com