
ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የፀጥታና ደኅንነት ኦፕሬሽን አካሄድን በተመለከተ ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡
የፀጥታና ደኅንነት ኦፕሬሽን አካሄድ ግምገማ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ እንዲሁም የክልልና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት በወሰነው መሰረት በኢትዮጵያ የህግ የበላይነትን በማስከበር የሕዝብ ደኅንነት ስጋትን ማስወገድ፣ ለውጭ ጠላት ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ ያለውን የውስጥ ተጋላጭነትን መቀነስ፣ እንዲሁም ሰላምን በማስፈን ልማትን ማረጋገጥን ታሳቢ ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው የታጠቁ ኀይሎችን በመለየት መልክ ማስያዝ፣ ታጥቀውና ተደራጅተው በህገወጥ መንገድ የተሰማሩ ፅንፈኛ ቡድኖችን ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲገቡ ማስቻልን ታሳቢ ያደረገ አቅጣጫ ማስቀመጡ ተነግሯል።
በዚህም የፀጥታ አካላት እንዲሁም የክልል አመራሮች የፀጥታና ደኅንነትን በማረጋገጡ ሂደት የተሠሩ ሥራዎች ተገምግመው ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥ ይሆናል መባሉን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/